Song Lyrics

ሃሌሉያ

Yosef Bekele
Balewuletaye Geta
አዝ፦ ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (4x) ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (4x) ዛሬም ተመስገን/ተባረክ የእኔ ጌታ ነገም ተመስገን/ተባረክ የእኔ አለኝታ ሁሌም ተመስገን/ተባረክ ለዘለዓለም እንዳንተ ያለ የለም አዎ (2x) እግዚአብሔር ኃያል ነህ ማንንም አትንቅም ማስተዋል ጥበብህ አይመረመርም ፍጥረት ሁሉ አንተን ሁሌ ያመስግኑህ የሚፈሩህ ሁሉ ለአንተ ይገዙልህ (3x) አዝ፦ ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (4x) ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (4x) ዛሬም ተመስገን/ተባረክ የእኔ ጌታ ነገም ተመስገን/ተባረክ የእኔ አለኝታ ሁሌም ተመስገን/ተባረክ ለዘለዓለም እንዳንተ ያለ የለም አዎ (2x) ዙፋንህ ጽኑ ነው የማትነቃነቅ ሽምግልና አያውቅህ ከቶ አትለዋወጥ ጥንት እንደሰራኸው ዛሬም ጸራለህ አትደክም አትታክት አንተ ያው አንተ ነህ (3x) አዝ፦ ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (4x) ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (4x) ዛሬም ተመስገን/ተባረክ የእኔ ጌታ ነገም ተመስገን/ተባረክ የእኔ አለኝታ ሁሌም ተመስገን/ተባረክ ለዘለዓለም እንዳንተ ያለ የለም አዎ (2x) በሰማይ በምድር ከምድር በታች ሁሉ ለታላቅነትህ ፍጥረታት ይስገዱ ያመስግኑህ ዛሬ ያንግሱህ በዕልልታ ንጉሥ ነህ ዘለዓለም የሰራዊት ጌታ (3x) አዝ፦ ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (4x) ሃሌሉያ (ሃሌሉያ) (4x) ዛሬም ተመስገን/ተባረክ የእኔ ጌታ ነገም ተመስገን/ተባረክ የእኔ አለኝታ ሁሌም ተመስገን/ተባረክ ለዘለዓለም እንዳንተ ያለ የለም አዎ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection