ማንም ያልፈታውን ማኅተም የፈታህ በትንሳዔው ጉልበት ሁሉንም የረታህ በአባቱ ቀኝ አለ መቃብር ፈንቅሎ ገና ሁሉን ይገዛል ዳግም ተመልሶ (2x) ኢየሱስ የነገሥታት ንጉሥ ኢየሱስ የጌቶቹ ጌታ ኢየሱስ በትንሳኤው ጉልበት ኢየሱስ ሁሉንም የረታ ከሥም ሁሉ በላይ ታላቅ ሥም አለው ለዚህ ሥም ማነው ማነው ማይገዛው ጉልበት ሁሉ ለእርሱ ይንበረከካል አጋንንት ለሥሙ ይንቀጠቀጣል ዛሬም ሕያው ነው ኢሄ አምላካችን ገናናው ኢየሱስ መከታ ጋሻችን (2x) መከታ ጋሻችን (2x) ሰባቱን ከዋክብት በእጁ የያዘ በወርቅ መታጠቂያ ደረቱን የታጠቀ እንደ እሳት ነበልባል ዓይኖቹ ይህ ጌታ ፊቱም እንደፀሐይ ደምቆ የሚያበራ (2x) ኢየሱስ የነገሥታት ንጉሥ ኢየሱስ የጌቶቹ ጌታ ኢየሱስ በትንሳኤው ጉልበት ኢየሱስ ሁሉንም የረታ ከሥም ሁሉ በላይ ታላቅ ሥም አለው ለዚህ ሥም ማነው ማነው ማይገዛው ጉልበት ሁሉ ለእርሱ ይንበረከካል አጋንንት ለሥሙ ይንቀጠቀጣል ዛሬም ሕያው ነው ኢሄ አምላካችን ገናናው ኢየሱስ መከታ ጋሻችን (2x) መከታ ጋሻችን (2x) የመጀመሪያና መጨረሻ እርሱ ነው ዘለዓለም ያው ሆኖ በላይ የሚኖረው የመክፈት የመዝጋት ሥልጣን ሁሉ የእርሱ በሆታ በዕልልታ ኢየሱስን አንግሱ ስሙን አወድሱ ኢየሱስ የነገሥታት ንጉሥ ኢየሱስ የጌቶቹ ጌታ ኢየሱስ በትንሳኤው ጉልበት ኢየሱስ ሁሉንም የረታ ከሥም ሁሉ በላይ ታላቅ ሥም አለው ለዚህ ሥም ማነው ማነው ማይገዛው ጉልበት ሁሉ ለእርሱ ይንበረከካል አጋንንት ለሥሙ ይንቀጠቀጣል ዛሬም ሕያው ነው ኢሄ አምላካችን ገናናው ኢየሱስ መከታ ጋሻችን (2x) መከታ ጋሻችን (2x) ውሃን አጣፈጠ ማዕበሉን አዘዘ በሙት በሲኦል ላይ ሥልጣኑን አሳየ ምን አለ በምድር ለእርሱ የተሳነው እኛም ምስክር ነን ኢየሱስ ጌታ ነው (2x) አቤት (4x) አቤት እንደኢየሱስ ማነው አቤት ኢየሱስ ጌታዬን እርሱን ማነው (ኧረ ማነው) እንደ ጌታ ማነው (ኧረ ማነው) እንደ ውዴ ማነው (ኧረ ማነው) እንደ ጌታ ማነው (ኧረ ማነው) እንደ ውዴ ማነው (ኧረ ማነው) እንደ ጌታ ማነው (ኧረ ማነው) እርሱ መድሃኒት ነው (ኧረ ማነው) እንደ ጌታ ማነው (ኧረ ማነው) እንደ ኢየሱስ ማነው (3x)