ዛሬ ልጅ ተብዬ ክብርን አግኝቻለሁ የቀድሞ ኑሮዬን ረስቼዋለሁ ታሪኬን ለውጠህ ሰው አድርጐ አቆመኝ የመረጥኩህ ልጄ እስራኤል ሆይ አለኝ የመረጥኩህ ልጄ የምወድህ ሆይ አለኝ አዝ፦ ኧረ ይህን ኢየሱስ ምን ብዬ ልባርከው ውለታው በዛብኝ ከአይምሮዬም በላይ ነው አቤት ምህረቱ ምን እከፍለዋለሁ እኔም ክብር አግኝቼ አገልጋል ሆኛለሁ ይኸው እድረስልኝ ዛሬም ምሥጋናዬ ኤሄሄ ማለት ችያለሁኝ እኔም አባብዬ (2x) በክርስትናዬ እድሜን ቆጥሬያለሁ በልማዳዊ ሕይወት ተመላልሻለሁ ዛሬ ግን ኢየሱስ ነፍሴ አወቀችህ አምላኬ ጌታዬ ውዴ ነህ አለችህ አምላኬ ጌታዬ አባቴ አለችህ አዝ፦ ኧረ ይህን ኢየሱስ ምን ብዬ ልባርከው ውለታው በዛብኝ ከአይምሮዬም በላይ ነው አቤት ምህረቱ ምን እከፍለዋለሁ እኔም ክብር አግኝቼ አገልጋል ሆኛለሁ ይኸው እድረስልኝ ዛሬም ምሥጋናዬ ኤሄሄ ማለት ችያለሁኝ እኔም አባብዬ (2x) የስቃይህን ሳስብ እንዲያው ስቅበዘበዝ ጠላት ቤቴ ገብቶ በጦር ሲበዘብዝ እርሱ ግን ጌታዬ አሰበኝ ለአንድ አፍታ ኃይሌም ተመለሰ ጠላቴም ተረታ ኃይሌም ተመለሰ ይክበር የእኔ ጌታ አዝ፦ ኧረ ይህን ኢየሱስ ምን ብዬ ልባርከው ውለታው በዛብኝ ከአይምሮዬም በላይ ነው አቤት ምህረቱ ምን እከፍለዋለሁ እኔም ክብር አግኝቼ አገልጋል ሆኛለሁ ይኸው እድረስልኝ ዛሬም ምሥጋናዬ ኤሄሄ ማለት ችያለሁኝ እኔም አባብዬ (2x)