Song Lyrics

ይሁን ሆይ

አዝ፦ ይሁን ሆይ (2x) ፈቃድህን ልጠይቅ ይሁን ሆይ የእኔ መንገድ የሚያምረው አንተ ቀድመህ ስትመራኝ ነው (2x) አንተ የሌለህበት ብራብ ላያጠግበኝ መንገዴም ላይቀና ሕይወት ላይሆንልኝ ልጠይቅ ፈቃድህን አባቴ ነህና እሾህ ማይኖረው መንገዴ ሲቀና (2x) አሃሃ በጐ መስሎኝ አሃሃ በዓይኔ አይቼ አሃሃ ተጐዳሁኝ አሃሃ ውስጥ ገብቼ አሃሃ ያየህልኝን አሃሃ እንድወርሰው አሃሃ ምራኝ ጌታ አሃሃ እንድደርሰው (2x) አዝ፦ ይሁን ሆይ (2x) ፈቃድህን ልጠይቅ ይሁን ሆይ የእኔ መንገድ የሚያምረው አንተ ቀድመህ ስትመራኝ ነው (2x) በሕይወቴ ስጓዝ ባለፉት ዘመናት ራሴን ሰምቼ ወጣሁኝ ለጥፋት ያኔ ይበቃኛል የሳትኩት መንገዴ ምራኝ እንደቃልህ በአንተ ይሁን ውዴ (2x) አሃሃ በጐ መስሎኝ አሃሃ በዓይኔ አይቼ አሃሃ ተጐዳሁኝ አሃሃ ውስጥ ገብቼ አሃሃ ያየህልኝን አሃሃ እንድወርሰው አሃሃ ምራኝ ጌታ አሃሃ እንድደርሰው (2x) አዝ፦ የእኔ መንገድ የሚያምረው አንተ ቀድመህ ጌታዬ ስትመራኝ ነው ይሁን ሆይ (2x) ፈቃድህን ልጠይቅ ይሁን ሆይ የእኔ መንገድ የሚያምረው አንተ ቀድመህ ስትመራኝ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection