የምድረበዳ ወዳጄ ነህ (አሃሃ) ሁሉን ያለፍኩብህ የምድረበዳ ወዳጄ ነህ (አሃሃ) ሁሉን ያረሳሁብህ ኧረ እኔ ኢየሱስ ያለአንተ አልኖርም (2x) እኔ ያለአንተ አልኖርም ኧረ እኔ ኢየሱስ ያለአንተ አልኖርም (2x) እኔ ያለአንተ አልኖርም (2x) ዓሣ ከሁሃ ውጭ እንደማይኖር እስትንፋስህ ርቆት ሕይወቴም ባዶ ነው የእኔ ጌታ አንተ የሌለህበት ሸካራው መንገዴን አለስልሰህ በፍቅር ይዘኸኝ ጥልቅህ ፍቅርህ ይዞ እየመራኝ በሕይወት አኖረኝ አስከፊውን መንገድ ሆነህ ከእኔ ጋራ በእጆችህ ይዘኸኝ እንዴት ልቤ ይፍራ (2x) ሲከፋኝ ስጨነቅ አጠገቤ ነህ ግራ ሲገባኝ ከጐኔ ምትቆም ሳትሰለቸኝ ምታበረታኝ የልጅነቴ አምላክ ምትሸከመኝ ከነማንነቴ የሕይወት ማብቂያ ነህ መደምደሚያዬ የመጨረሻዬ አስከፊውን መንገድ ሆነህ ከእኔ ጋራ በእጆችህ ይዘኸኝ እንዴት ልቤ ይፍራ (2x) የምድረበዳ ወዳጄ ነህ (አሃሃ) ሁሉን ያለፍኩብህ የምድረበዳ ወዳጄ ነህ (አሃሃ) ሁሉን ያረሳሁብህ ኧረ እኔ ኢየሱስ ያለአንተ አልኖርም (2x) እኔ ያለአንተ አልኖርም ኧረ እኔ ኢየሱስ ያለአንተ አልኖርም (2x) እኔ ያለአንተ አልኖርም (2x)