አዝ፦ ሃሌሉያ (4x) ከኀጢአት ባርነት ከዘለዓለም ሞት አዳነን ኢየሱስ እኛን ሰጠን ሕይወት ፍፁም አምላክ ሲሆን እራሱን አዋረደ የባሪያውን መልክ ይዞ ከሰማይ ወረደ በጠና. (1) . ከስፍራው በበረት ተወለደ ስለኀጢአተኞች ስለእኛ ማለደ አዝ፦ ሃሌሉያ (4x) ከኀጢአት ባርነት ከዘለዓለም ሞት አዳነን ኢየሱስ እኛን ሰጠን ሕይወት በመስቀል ላይ ለመሞት ፈቃደኛውን ከዘለዓለም ሞት ሊያድንን ከኩነኔ የጥልቅ ግድግዳውን በሥጋው አፈረሰ ለኀጢአት ይቅርታ ደሙን አፈሰሰ አዝ፦ ሃሌሉያ (4x) ከኀጢአት ባርነት ከዘለዓለም ሞት አዳነን ኢየሱስ እኛን ሰጠን ሕይወት ሰላሳ ሶስት አመት በምድር ላይ ኖረ የሕይወትን መንገድ ለሰዎች አስተማረ የሁሎችን በደል እርሱ ተሸከመ አገልግሎቱን በመስቀል ላይ ፈጸመ አዝ፦ ሃሌሉያ (4x) ከኀጢአት ባርነት ከዘለዓለም ሞት አዳነን ኢየሱስ እኛን ሰጠን ሕይወት