Song Lyrics

በውኃ ውስጥ አልፈናል

Workneh Alaro
Ke Esat Wust Yenetekegn
አዝ፦ በውኃ ውስጥ አልፈናል አላሰጠመንም ኦ ይገርማል ኦ ይደንቃል በእሳት ውስጥ ሄደናል አላቃጠለንም ኦ ይገርማል ኦይደንቃል ባለፍንበት መንገድ የጠበቀን ያሻገረን እግዚአብሔር ይመስገን እስከዚች ቀን ድረስ የጠበቀን የደረሰልን እግዚያብሄር ይመስገንልን በሁሉ ላይ ስልጣን ያለው ጌታ በቃልህና በስራህ የበረታህ በጉልበቱ ፅናት የሚራመድ ጥልቁን ባሕር አረገልን መንገድ ያንን ባሕር አደረገልን መንገድ አዝ፦ በውኃ ውስጥ አልፈናል አላሰጠመንም ኦ ይገርማል ኦ ይደንቃል በእሳት ውስጥ ሄደናል አላቃጠለንም ኦ ይገርማል ኦይደንቃል ባለፍንበት መንገድ የጠበቀን ያሻገረን እግዚአብሔር ይመስገን እስከዚች ቀን ድረስ የጠበቀን የደረሰልን እግዚያብሄር ይመስገንልን ምንም ያህል እሳት ቢነድም የመከራ እቶን ቢያይልም እግዚአብሔር የተባዥው አስተማማኝ ማምለጫ አለው አስተማማኝ ማለፊያ አለው አዝ፦ በውኃ ውስጥ አልፈናል አላሰጠመንም ኦ ይገርማል ኦ ይደንቃል በእሳት ውስጥ ሄደናል አላቃጠለንም ኦ ይገርማል ኦይደንቃል ባለፍንበት መንገድ የጠበቀን ያሻገረን እግዚአብሔር ይመስገን እስከዚች ቀን ድረስ የጠበቀን የደረሰልን እግዚያብሄር ይመስገንልን እንደአገኘን መከራ ብዛት እንደነደደው እሳት ብርታት እስከዛሬ ዘር አልባ አልቀረንም እግዚአብሔር ግን ይልቅ አበዛን እግዚአብሔር ግን በጤና አኖረን አዝ፦ በውኃ ውስጥ አልፈናል አላሰጠመንም ኦ ይገርማል ኦ ይደንቃል በእሳት ውስጥ ሄደናል አላቃጠለንም ኦ ይገርማል ኦይደንቃል ባለፍንበት መንገድ የጠበቀን ያሻገረን እግዚአብሔር ይመስገን እስከዚች ቀን ድረስ የጠበቀን የደረሰልን እግዚያብሄር ይመስገንልን
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection