Song Lyrics

እግዚአብሔር አለ

Workneh Alaro
Ke Esat Wust Yenetekegn
የአብርሃም የይስሃቅ የያዕቆብ አምላክ ዛሬም በቅዱስ ማደሪያው አለና ሥጋ ለባሽ ሁሉ በፊቱ ዝም ይበል እግዚአብሔር አለና አዝ፦ የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ለዘለዓለምም ነዋሪ ማይደክም ማይታክተዉ ማስተዋሉ ማይመረመረዉ እግዚአብሔር አለ በማደሪያው እግዚአብሔር አለ በከፍታው ለደካማ ኃይልን ይሰጣል ጉልበት ላጣው ብርታት ይጨምራል በጽድቁ ቀን ደግፎ ይይዛል እግዚአብሔር ህዝቡን መቼ ይተዋል (2x) አዝ፦ የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ለዘለዓለምም ነዋሪ ማይደክም ማይታክተዉ ማስተዋሉ ማይመረመረዉ እግዚአብሔር አለ በማደሪያው እግዚአብሔር አለ በከፍታው ውሆችን በእፍኙ የሰፈረ ሠማይን በስንዝር የለካዉ ከፍ ባለ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ነው አዝ፦ የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ለዘለዓለምም ነዋሪ ማይደክም ማይታክተዉ ማስተዋሉ ማይመረመረዉ እግዚአብሔር አለ በማደሪያው እግዚአብሔር አለ በከፍታው ስለድሆች መከራ ስለችግረኞች ጩኸት ጌታዬ ይመጣል ወደመቅደሱ በድንገት የወደቀ ይነሳል የሳተ ይመለሳል በእግዚአብሔር ጉብኝት ገና ጠላት ይቃጠላል ተስፋ የቆረጣችሁ በእምነት ደክማችሁ በጠላትም ዛቻ አንገት የደፋቹህ አምላካቹህ በበቀል በእርግጥ ይመጣል የእናንተም ደስታ ገና እስከ ሩቅ ይሰማል ያዕቆብ ሆይ እስራኤልም ሆይ አልሰማህም ወይ አላወቅክም ወይ (2x) መንግዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ ደግሞም አልፋለች ለምን ትላለህ ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ አልሰማህም ወይ አላወክህም ወይ የእኛ ጌታ አለ (አለ) እንደነገሠ (አለ) አላረጀም (አለ) አልደከመም (አለ) አይታክትም (አለ) አለ ጌታ (አለ) አለ ጌታ (አለ) ትናንትናም ዛሬም (አለ) ነገም ለዘለዓለም (አለ) ያው ነው ኢየሱስ (አለ) አለ ጌታ (አለ) አለ ጌታ (አለ) አለ ውዴ (አለ) አለ ጌታ (አለ አለ)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection