Song Lyrics

ከእሳት ውስጥ የነጠቀኝ

Workneh Alaro
Ke Esat Wust Yenetekegn
አዝ፦ ከእሳት ውስጥ የነጠቀኝ በሕይወት ኑር ያለኝ ያዳነኝ ኢየሱስ ነው (2x) የራራልኝ ኢየሱስ ነው አበሳዬን ሁሉ አራቀ እድፋሙን ልብሴን ቀየረው (2x) ሰይጣንን ገሰጸው እርሱ እኮ ልጄ ነው አለው የእኔ ነው ብሎ አባረረው አዝ፦ ከእሳት ውስጥ የነጠቀኝ በሕይወት ኑር ያለኝ ያዳነኝ ኢየሱስ ነው (2x) የራራልኝ ኢየሱስ ነው ጠላት ዘባበተብኝ አምላክህ እስቲ ያድንህ አለኝ መጨረሻህ ዛሬ ነው አለኝ የተዋረዱትን የሚያይ ከተፍ አለልኝ ከሰማይ እንደእርሱ ማነው ኤልሻዳይ አዝ፦ ከእሳት ውስጥ የነጠቀኝ በሕይወት ኑር ያለኝ ያዳነኝ ኢየሱስ ነው (2x) የራራልኝ ኢየሱስ ነው እግዚአብሔር ለካ መልስ አለው ዙሪያዬን ለከበበኝ ሊወግረኝ ድንጋይ ላነሳን አቤት የማዳን ጥበቡ የማይመረመር ነው ፍርዱ በዕልልታ ለእርሱ ስገዱ አዝ፦ ከእሳት ውስጥ የነጠቀኝ በሕይወት ኑር ያለኝ ያዳነኝ ኢየሱስ ነው (2x) የራራልኝ ኢየሱስ ነው ሰይጣን በብርቱ ከሰሰኝ በኀጢአቴ እንዲፈረድብኝ ____ እንዲ ከከበበ ጠበቃዬ ኢየሱስ ቆመልኝ በደሙ አስተሰረየልኝ (2x) አዝ፦ ከእሳት ውስጥ የነጠቀኝ በሕይወት ኑር ያለኝ ያዳነኝ ኢየሱስ ነው (2x) የራራልኝ ኢየሱስ ነው
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection