Song Lyrics

ታላቅና የተፈራህ

Workneh Alaro
Ke Esat Wust Yenetekegn
እልፍ አእላፋት መላዕክት ከፊትህ እየሰገዱ ቅዱስ ቅዱስ እያሉ ሁሌ የሚያመልኩህ በረከትና ክብር ምሥጋናም ሃይልም ለአንተ ለቅዱሱ ይሁን ለዘለዓለም አዝ፦ ታላቅና የተፈራህ አምላክ በቅድስናህ የከበርህ ጌታ ከፍ ካለ ዙፋን ላይ በከፍታ ያለህ ቅዱስ (3x) እግዚአብሔር በሰማይና በምድር ታላቁ ስምህ ይክበር ከዘመናት ሁሉ ክብርህን ጠብቀህ ሳትሻር ሳትለወጥ በዙፋንህ ጸንተህ ያለህና የነበርህ ሁሉን ምትገዛ አምላክ በምሥጋና ከፍ ያለው ክቡር ስምህ ይባረክ አዝ፦ ታላቅና የተፈራህ አምላክ በቅድስናህ የከበርህ ጌታ ከፍ ካለ ዙፋን ላይ በከፍታ ያለህ ቅዱስ (3x) እግዚአብሔር በሰማይና በምድር ታላቁ ስምህ ይክበር ማለዳ እጅግ ተሞልቶ ከክብርህ ታላቅነት አምልኮ ለአንተ ይቀርባል ዘወትር ቀንና ሌሊት ሃያልና ባለብዙ ግርማ ሞገስ እንደአንተ የለምና ለዘለዓለም ንገሥ አዝ፦ ታላቅና የተፈራህ አምላክ በቅድስናህ የከበርህ ጌታ ከፍ ካለ ዙፋን ላይ በከፍታ ያለህ ቅዱስ (3x) እግዚአብሔር በሰማይና በምድር ታላቁ ስምህ ይክበር ልጽሆም ልጽህር የፈቀድከውን ልታደርግ ሃይልና ስልጣን ያለህ የወሰንከውን ልትፈጽም አማካሪና ረዳት ከቶ የማያስፈልግህ ምንም የማይጐድልህ ፍፁም አምላክ አንተ ነህ አዝ፦ ታላቅና የተፈራህ አምላክ በቅድስናህ የከበርህ ጌታ ከፍ ካለ ዙፋን ላይ በከፍታ ያለህ ቅዱስ (3x) እግዚአብሔር በሰማይና በምድር ታላቁ ስምህ ይክበር
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection