Song Lyrics

እንዴት እንዲያድን ያውቃል እግዚአብሔር

Workneh Alaro
Ke Esat Wust Yenetekegn
አዝ፦ እንዴት እንዲያድን ያውቃል እግዚአብሔር (2x) እንዴት እንዲያስመልጥ ያውቃል እግዚአብሔር (2x) እንዴት እንዲያድን ያውቃል እግዚአብሔር (2x) እንዴት እንዲያስመልጥ ያውቃል እግዚአብሔር (2x) የሚያመልኩትን የእርሱ የሆኑትን በፈተና ሆነው የሚያለቅሱትን (2x) አመጻ ቢጀመር ምናምንቴ በዝቶ ጻድቅ ቢከበብ ጠላት አንሰራርቶ በአመጸኞች ኑሮ ያን የተገፋውን ሊያድን ይመጣል እግዚአብሔር ባሪያውን (2x) አዝ፦ እንዴት እንዲያድን ያውቃል እግዚአብሔር (2x) እንዴት እንዲያስመልጥ ያውቃል እግዚአብሔር (2x) እንዴት እንዲያድን ያውቃል እግዚአብሔር (2x) እንዴት እንዲያስመልጥ ያውቃል እግዚአብሔር (2x) የሚያመልኩትን የእርሱ የሆኑትን በፈተና ሆነው የሚያለቅሱትን (2x) ድብልቅ ህዝብ ነው በግብጽ የወጣው የእግዚአብሔርን ወገን መለየት ከባድ ነው ቢሆንም አምላኬ የእርሱ የሆኑትን ያውቃል ማውረስ ያለበትን ትውልድ ያሻግራል (2x) አዝ፦ እንዴት እንዲያድን ያውቃል እግዚአብሔር (2x) እንዴት እንዲያስመልጥ ያውቃል እግዚአብሔር (2x) እንዴት እንዲያድን ያውቃል እግዚአብሔር (2x) እንዴት እንዲያስመልጥ ያውቃል እግዚአብሔር (2x) የሚያመልኩትን የእርሱ የሆኑትን በፈተና ሆነው የሚያለቅሱትን (2x) እግዚአብሔር ባርያውን ማንም አይጐዳም ከእሳት ውስጥ ሲመጣ ያኔ ምልክት አያልፍም የማምለጫ አለት ነው በእርግጥ ያስመልጣል በእርሱ ያመነን መቼ ያሳፍራል (2x) አዝ፦ እንዴት እንዲያድን ያውቃል እግዚአብሔር (2x) እንዴት እንዲያስመልጥ ያውቃል እግዚአብሔር (2x) እንዴት እንዲያድን ያውቃል እግዚአብሔር (2x) እንዴት እንዲያስመልጥ ያውቃል እግዚአብሔር (2x) የሚያመልኩትን የእርሱ የሆኑትን በፈተና ሆነው የሚያለቅሱትን (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection