አዝ፦ አቤቱ ፈውሰን እኛም እንፈወሳለን አቤቱ መልሰን እኛም እንመለሳለን (2x) ቃልኪዳንና ሚሉትን የምትጠብቅ ታላቅና ሃያል የተፈራህ አምላክ በደረሰብን ነገር ሁሉ አንተ ጻዲቅ ነህ ቤትህን መልስልን ጉስቁልናችንን አይተህ አዝ፦ አቤቱ ፈውሰን እኛም እንፈወሳለን አቤቱ መልሰን እኛም እንመለሳለን (2x) እንደበደላችን አታድርግብን እንደኀጢአታችንም አትክፈለን እጠበን ጌታ ሆይ እኛም እንነጻለን ከበረዶ ይልቅ ነጭ እንሆናለን አዝ፦ አቤቱ ፈውሰን እኛም እንፈወሳለን አቤቱ መልሰን እኛም እንመለሳለን (2x) በብዙ እንግዳ ነገር ረክሰናል የተወደደው እርሻ በባሕር ተረግጧል ጠላትም በቤትህ ጓዳ ይኖራል የተቀደሰው እቃ ለብዝበዛ ሆኗል አዝ፦ አቤቱ ፈውሰን እኛም እንፈወሳለን አቤቱ መልሰን እኛም እንመለሳለን (2x) ከአመጻችን ብዛት መንፈስህን አስመረርን እጅግ አስቆጣንህ በእምቢተኝነታችን አንተ ግን ምህረትህ የበዛ አምላክ ነህ ታደገን አባት ሆይ ስለስምህ ብለህ አዝ፦ አቤቱ ፈውሰን እኛም እንፈወሳለን አቤቱ መልሰን እኛም እንመለሳለን (2x)