Song Lyrics

ነፍሴ ሆይ

Workneh Alaro
Ke Esat Wust Yenetekegn
የአብርሃም የይሳቅ የያዕቆብ አምላክ ዛሬም በቅዱስ ማደሪያው አለና ሥጋ ለባሽ ሁሉ በፊቱ ዝም ይበል እግዚአብሔር አለና እግዚአብሔር አለና አዝ፦ የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ለዘለዓለምም ነዋሪ ማይደክም ማይታክተው ማስተዋሉ ማይመረመረዉ እግዚአብሔር አለ በማደሪያው እግዚአብሔር አለ በከፍታው ልደካማ ሃይልን ይሰጣል ጉልበት ላጣው ብርታት ይጨምራል በጽድቁ ቀን ደግፎ ይይዛል እግዚአብሔር ህዝቡን መቼ ይተዋል (2x) አዝ፦ የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ለዘለዓለምም ነዋሪ ማይደክም ማይታክተው ማስተዋሉ ማይመረመረዉ እግዚአብሔር አለ በማደሪያው እግዚአብሔር አለ በከፍታው ወፎችን በእፍኙ የሰፈረው ሰማይን በስንዝር የለካው ከፍ ባለ ዙፋን ላይ የተቀመጠው ለትውልድ ሁሉ መጠጊያ ነው አዝ፦ የምድር ዳርቻ ፈጣሪ ለዘለዓለምም ነዋሪ ማይደክም ማይታክተው ማስተዋሉ ማይመረመረዉ እግዚአብሔር አለ በማደሪያው እግዚአብሔር አለ በከፍታው ስለደሆች መከራ ስለችግረኞች ጌታዬ ይመጣል ወደመቅደሱ በድንገት የወደቀ ይነሳል የሳት ይመለሳል በግዚአብሄር ጉብኝት ገና ጠላት ይቃጠላል ተስፋ የቆረጣችሁ በእምነት የደክማችሁ በጠላትም ዛቻ አንገት የደፋቹህ አምላካቹህ በበቀል በእርግጥ ይመጣል የእናንተም ደስታ ገና ከሩቅ ይሰማል ያዕቆብ ሆይ እስራኤልም ሆይ አልሰማህም ወይ አላወቅህም ወይ (2x) መንገዴ ከእግዚአብሔር ተሰውራለች ፍርዴም ከአምላኬ ደግሞም አልፋለች ለምን ትላለህ ለምንስ እንዲህ ትናገራለህ አልሰማህም ወይ አላወቅህም ወይ የኛ ጌታ አለ (አለ) እንደነገሠ (አለ) አላረጀም (አለ) አልደከመም (አለ) አይታክትም (አለ) አለ ጌታ (አለ) አለ ጌታ (አለ) ትላንትናም ዛሬ (አለ) ነገም ለዘለዓለም (አለ) ያው ነው ኢየሱስ (አለ) አለ ጌታ (አለ) አለ ጌታ አለ ውዴ (አለ) አለ ጌታ (አለ)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection