Song Lyrics

እንደተሰጠህ አገልግል

Workneh Alaro
Amelkewalew
ደረት እየደቁ የተከተሉትን እናንተ የኢየሩሳሌም ሴቶች ለራሳችሁ አልቅሱ ብሎ መልሶ የተዘባበቱበትንም ሁሉ በመስቀል ላይ ጭምር ታግሶ የመዳናችንም ራስ በመከራ የፈጸመውን ጌታ ተመልክተን በተሰጠን ፀጋ በታማኝነት ለማገልገል እንበርታ አዝ፦ እንደ ተሰጠህ አገልግል ከሠማይ የሆነውን አደራ ችላ አትበል ከሚያገሰግኑ አፍ እንዳትፈተን ልብህን አትጣ በተቃዋሚዎችም ተደናግጠህ ፈቀቅ እንዳትል የጠራህን ጌታ እያየህ ሩጫውን ቀጥል ከአፉ የሚወጣው ቃል ይሁን መኖሪያ የተጻፈው ለትምህርት ይሁን መመሪያ የላከህ ያለህን ሁሉ ያደረገ ዳግመኛ ሲመለስ ጌታ እንዲያገኝህ የጊዜው ስካር ከዓላማህ እንዳያስትህ ንቃ ተጠበቅ አደራ እንዳያስጥል አዝ፦ እንደ ተሰጠህ አገልግል ከሠማይ የሆነውን አደራ ችላ አትበል ከሚያገሰግኑ አፍ እንዳትፈተን ልብህን አትጣ በተቃዋሚዎችም ተደናግጠህ ፈቀቅ እንዳትል የጠራህን ጌታ እያየህ ሩጫውን ቀጥል ዓለምን አትርፎ ነፍሱን ባያጐድል ከአገለገለ በኋላ ራሱ እንዳይጣል ሥጋውን እየጐሰመ ለጌታ ያስገዛል እንጂ ራሱን መቼ ይሰብካል አስተዋይ የማልጠቅም ባሪያ ነኝ ይላል ክብርን ሁሌ ለጌታ ያስረክባል አዝ፦ እንደ ተሰጠህ አገልግል ከሠማይ የሆነውን አደራ ችላ አትበል ከሚያገሰግኑ አፍ እንዳትፈተን ልብህን አትጣ በተቃዋሚዎችም ተደናግጠህ ፈቀቅ እንዳትል የጠራህን ጌታ እያየህ ሩጫውን ቀጥል የልብሳቸውን ዘርፍ አስረዝመው አሸ. (1) . ሲያሰፉ ጾመኛ መስለው ሊታዩ ለሰዎች ፊታቸውን ሲያጠፉ አሥራት መጿት ሲያወጡ መለከት ሲያስነፉ ግብዞች ልብን በሚያይ ጌታ . (2) . የመንግሥቱ ሠማያት ደቀመዝሙር በእውንት ራሱን ይመርምር አዝ፦ እንደ ተሰጠህ አገልግል ከሠማይ የሆነውን አደራ ችላ አትበል ከሚያገሰግኑ አፍ እንዳትፈተን ልብህን አትጣ በተቃዋሚዎችም ተደናግጠህ ፈቀቅ እንዳትል የጠራህን ጌታ እያየህ ሩጫውን ቀጥል
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection