Song Lyrics

እግዚአብሔር ብቻውን

Workneh Alaro
Amelkewalew
አዝ፦ እግዚአብሔር ብቻውን መርቶ በፀናች ክንድ በድል ረትቶ የምታስፈራውን ምድረበዳ ተሸገርን በጌታ ሳንጎዳ የፈራናትንም ምደረበዳ ተሸገርን በእግዚአብሔር ሳንጎዳ አማሌቅ በመንገድ ተቃወመን ደክመን ሳለን መንገድ ዘጋጋብን ተዋጊው እግዚአብሔር ድል አድርጎልን ስንት ጭንቅ መንገዶችን አለፍን ተዋጊው ወዳጄ ፊት ቀድሞልን ስንት ጭንቅ መንገዶችን አለፍን አዝ፦ እግዚአብሔር ብቻውን መርቶ በፀናች ክንድ በድል ረትቶ የምታስፈራውን ምድረበዳ ተሸገርን በጌታ ሳንጎዳ የፈራናትንም ምደረበዳ ተሸገርን በእግዚአብሔር ሳንጎዳ እርምጃችንን ሊያሰናክሉ የመከሩ የክፋት ሰራዊት መጥመድን ሰወሩ በመንገዳችን ላይ እንቅፋት አኖሩ ጌታ ደርሶልን ፈረሰ ምክሩ (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር ብቻውን መርቶ በፀናች ክንድ በድል ረትቶ የምታስፈራውን ምድረበዳ ተሸገርን በጌታ ሳንጎዳ የፈራናትንም ምደረበዳ ተሸገርን በእግዚአብሔር ሳንጎዳ ከአውሬ ጋር ብዙ ጊዜ ታግለናል ስለነፍሳችን እንኳን ተስፋ ቆርጠናል በብርቱ ሰልፍ መሀል ክንዱን አይተናል በአምላካችን ብርታት ቅጥሩን ዘለናል (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር ብቻውን መርቶ በፀናች ክንድ በድል ረትቶ የምታስፈራውን ምድረበዳ ተሸገርን በጌታ ሳንጎዳ የፈራናትንም ምደረበዳ ተሸገርን በእግዚአብሔር ሳንጎዳ የጨካኞች ቁጣ እስትንፋስ ቅጥርን እንደሚመታ አውሎንፋስ ባየለበት ዘመን በእርሱ ድል አድርገናል በክንዱ ፅናት ከሁሉ ተርፈናል (2x) አዝ፦ እግዚአብሔር ብቻውን መርቶ በፀናች ክንድ በድል ረትቶ የምታስፈራውን ምድረበዳ ተሸገርን በጌታ ሳንጎዳ የፈራናትንም ምደረበዳ ተሸገርን በእግዚአብሔር ሳንጎዳ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection