አዝ፦ አመልክሃለሁ ብቻውን አምላክ ነው (2x) አመልከዋለሁ የማይጠፋው የዘመናት ንጉሥ ኢየሱስ ነው አመልከዋለሁ የወደደኝ በደሙ ያጠበኝ አንድዬ ነው አመልከዋለሁ በማንም የማለውጠው ውድ ወዳጄ ነው አመልክሃለሁ ጌታዬም አምላኬም እርሱ ነው አመልከዋለሁ ስለእኔ ነፍሱን የሰጠ ሌላ ማነው አመልከዋለሁ ጌታዬም አምላኬም እርሱ ነው አመልከዋለሁ ስለእኔ በመስቀል የሞተ ሌላ ማነው ስለእኔ በመስቀል የሞተ ማነው ከአንተ ሌላ ማነው ማነው የሚታዩትና የማይታዩትም ዙፋናትህ (2x) ጌትነት ወይም አለቅነት ሥልጣናት በሠማይና በምድር ያሉት ፍጥረት ሁሉ (2x) በእርሱ ተፈጥረዋል ኧረ እርሱ ፍጡር አይደለም በኢየሱስ ተፈጥረዋል ወዳጄ ፍጡር አይደለም ዲያቢሎስ የተቀላቀለ ነገር ቢሰብክም ክርስትና መገለጥ ነው አልታለልም የእግዚአብሔርን የክብሩን እውቀት ብርሃን በውስጤ ጨለማን ያበራ ጌታ ይመስገን በእግዚአብሔርና በሰውም መካከል ያለው መካከለኛው (2x) አንድ ነው እርሱም ሰው የሆነው ክርስቶስ ነው ነፍሱንም ለሁሉ ቤዛ የሰጠው የሰጠ መልክተኛ ብቻ አይደለም መዳን/ሕይወት በእርሱ ነው (2x) ብቻም ብዙ አማልክትና ብዙ ጌቶች አሉ ጌታዬ አይደሉም በውሸት ዕውቀት ሰውን ያታለሉ ሠማይም ቢሆን በምድር ላይ ከአማልክት አሉ ኢየሱስ ብቻ ነው አዳኝ የተቀባ አዳኝ እውነቱ ሲታይ አዝ፦ አመልክሃለሁ ብቻውን አምላክ ነው (2x) አመልከዋለሁ የማይጠፋው የዘመናት ንጉሥ ኢየሱስ ነው አመልከዋለሁ የወደደኝ በደሙ ያጠበኝ አንድዬ ነው አመልከዋለሁ በማንም የማለውጠው ውድ ወዳጄ ነው አመልክሃለሁ ጌታዬም አምላኬም እርሱ ነው አመልከዋለሁ ስለእኔ ነፍሱን የሰጠ ሌላ ማነው አመልከዋለሁ ጌታዬም አምላኬም እርሱ ነው አመልከዋለሁ ስለእኔ በመስቀል የሞተ ሌላ ማነው ስለእኔ በመስቀል የሞተ ማነው ከአንተ ሌላ ማነው ማነው