Song Lyrics

ማራናታ

Tilahun Goa
Metawekiyaye
መምጫው ቀርቧል ሰዓቱ ደርሷል *2 ንቃ ወገኔ ሆይ ንቃ *2 ንቂ ሆይ ንቂ *2 የተናገርከን ተፈጽሟል ሰዓቱ ደርሷል ፊትህን ብቻ ለማየት እጅግ ናፍቀናል መቼ እናያለን የሰማዩን ቤታችንን መርሻችን ይፍጠን የምድር ኑሮ ጭንቀታችንን አሳርፈን እባክህን ገላጋያችን ከዚህ ዓለም ስቃይ ከችግራችን ምጽአትህን ብቻ እንጠብቃለን አንድ ቀን ስትመጣ አንድ ቀን ስትመጣ እንሄዳለን ኢየሱስ ሆይ ና *3 መከራችን በዝቷልና *2 የምንሰማው መልካም አይደለም ዕለት ዕለት ቀንም ከቀን እየከፋ ነው ይበዛል ድንገት ምድራችን ተሞልታለች ክፋትና እርኩሰት የሚማማል ብዙ ነው ወገንን ለማጥፋት ቶሎ ና *6 ወንድም ወንድሙን ገድሎ ከቀበረ ባል ሚስቱን ደግሞ ገድሏት ካሳደረ በቃሉ ሲፈተሽ ይህ ነው ሰዓቱ እነሆ በደጃችን ነው ዳግም ምጽዓቱ ደርሷል ሰዓቱ *2 የጌታ ዳግም ምጽዓቱ *2 የጌታ ዳግም ምጽዓቱ መንግስት በመንግስት ላይ ተነስቷል ለውጊያ ዘወትር የሚሰማው የነፍስ ግድያ እንደ ጎርፍ ይፈሳል የሰው ደም በምድር ሁከትና ረብሽ ሆኗል በብዙ መንደር ምነው ጌታ ሆይ በመጣህ ያልኳቸው ቀናቶች እነሆ እጅግ ብዙ ናቸው ጊዜም ከጊዜ ይልቅ እየከፋ ነው በእርግጥ ይህማ የጌታ መምጫ ነው ቶሎ ና *3 ናፍቀንሃልና ደርሷል ሰዓቱ የጌታ ዳግም ምፅዓቱ *2 የጌታ ዳግም ምፅዓቱ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection