Song Lyrics

አሻገረኝ

Tilahun Goa
Metawekiyaye
የመጣው ፈተና ከአቅሜ በላይ ከቶ አያስቀረኝም ከመንግስተ ሰማይ የገሃነም ደጆች አይችሉኝምና ኃይል አለኝ ዛሬም ሄዳለሁ ጥሼ ጥሼ ገና ከገጠመኝ ዉጊያ ከጠላት ፈተና ጌታ አሻገረኝ ሁሉን ቻይ ነውና በደከምኩኝ ጊዜ ቆሞ ከአጠገቤ አትፍራ ስላለኝ ብርቱ ሆኗል ልቤ ብርቱ ሆኗል ልቤ*4 አሻገረኝ*3 ጌታ አሻገረኝ አሻገረኝ*3 ጌታ አሻገረኝ ጌታ አሻገረኝ *3 አለሁልህ እያለኝ ጌታ አሻገረኝ *3 አለሁልህ እያለኝ ሕይወት ሆኖለታል ለደረቁ አጥንቴ ብርታት ለቆበታል በዛለው ጉልበቴ ማን ነበርኩኝ እኔ ባይረዳኝ አባቴ በርሱ ፀንቶ ቆሟል ያዘመመው ቤቴ ያዘመመው ቤቴ*4 እኔ አለሁ በጤና*6 ሞቴን የተመኘው ጠላቴ ሲበላ ከአመት ዓመት ከዘመን ዘመን በሰላም ጠብቆ ያሸጋገረኝ መድኃኒዓለም ከፍ ይበልልኝ *9 ጠላት ሲያባርረኝ ሊይዘኝ ከኋላ በትር ስዘረጋ ተገኝቶኛል መላ በደረቁ ምድር እኔን አሳልፎ የሚከተለኝን ጠላት ሬሳውን አንሳፍፎ ሬሳውን አንሳፍፎ*4 ለቅሶ ዋይታ እንዲሆን ሁሌም በእኔ ቤት ሲሟርት ሲመትት እንዳልኖር እንድሞት ጨርቁን ጥሎ አበደ ሞቴን የተመኘ የበቀል ዘመን ነው ለካ የመሸጋገሬ እኔ አለሁ በጤና*6 ሞቴን የተመኘው ጠላቴ ሲበላ ከአመት ዓመት ከዘመን ዘመን በሰላም ጠብቆ ያሸጋገረኝ መድኃኒዓለም ከፍ ይበልልኝ *9 ላሻገረኝ ለዚህ ጌታ ምስጋናዬ ለርሱ ይግባ ላበሰልኝ የአይኔን እማባ አምልኮዬ ለርሱ ይግባ ለርሱ ይግባ *4 ለዚህ ጌታ ለርሱ ይግባ *4
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection