ትላንትን አልፌ ዛሬን ማግኘቴ የምናገረው አለኝ እስኪ እኔ በደካማው ጎኔ ቆመህልኝ አይዞህ ልጄ እያልከኝ መድህኔ ተሻግሬአለሁኝ ብዙ ምድረበዳን በአንተ ገደላገደሉን አለፍኩኝ ሆነኸኝ ጉልበቴ እንዴት ተብሎ ይረሳል ውለታህ *4 አይረሳም የውለታ የዋልክልኝ በጎልጎታ ህዝብህ ሁሉ አፍ አውጥቶ ያመስግንህ ክብሩን ጥሎ *2 ዘላለም አልረሳም*3 ምን ጊዜም አልረሳም *3 ሞቴን የጠበቁት መክበሬን ሰምተዋል ውድቀቴን ያለሙት መቆሜን አይተዋል የሚልህ ይሄ ነው ለውለታህ ብዛት ይግባህ ከማደሪያ የምስጋና መስዋዕት አይረሳም የውለታ የዋልክልኝ በጎልጎታ ህዝብህ ሁሉ አፍ አውጥቶ ያመስግንህ ክብሩን ጥሎ *2 ሰው ከተረፈው ነገር ለሌላው ይሰጣል ስለ ሃጢያተኛ ማን ነፍሱን ይሰዋል ፍቅር የባሰበት በደሙ ገዝቶኛል በመስቀሉ ላይ ሆኖ አ አማልዶልኛል *2 እንዴት ተብሎ ይረሳል ውለታህ*4 አይረሳም የውለታ የዋልክልኝ በጎልጎታ ህዝብህ ሁሉ አፍ አውጥቶ ያመስግንህ ክብሩን ጥሎ *2 ዘላለም አልረሳም *3 ምን ጊዜም አልረሳም *3 ውስጤ የማይረሳው አለብኝ ውለታ በመስቀል እንደ ሌባ ስለኔ የተወጋ ጎልጎታ አናት ላይ ተመተህ ደካክመህ ልጅህ አድርገሀኛል ነፍሰህን ሰዉተህ ኸረ/ታዲያ እንዴት እረሳለሁ ይህን ያንተን ውለታ የሆንክልኝ መዳኒት ከኃጢአት በሽታ አይረሳም የውለታ የዋልክልኝ በጎልጎታ ህዝብህ ሁሉ አፍ አውጥቶ ያመስግንህ ክብሩን ጥሎ *2 ዘላለም አልረሳም *3 ምን ጊዜም አልረሳም *3 እኔ አልረሳም