Song Lyrics

መታወቂያዬ

Tilahun Goa
Metawekiyaye
ሰዎች ሲጠሩበት ባላቸው በሀብት መታወቂያቸው ሆኖ ምጠፋው ንብረት ለኔ ለታናሹ ገብቶኝ አንድ እውነት አዳኜ ኢየሱስ ሆኖኝ ምልክት መታወቂያዬ እያልኩህ በራሴ ህይወት አንጎራጉራለሁ በቀን በምሽት *2 መታወቂያዬ ልበልህ መታወቂያዬ መታወቂያዬ ልበልህ የዘላለሜ በአንተ ብቻ ይሁን የኔ ድምዳሜ *2 ልቤ እንዳይረባብሽ ባንተ እንዲረጋጋ ቃልህን ልማረው ወደ አንተ ልጠጋ በሆይ ሆይታ እንዳያልቅ በከንቱ ዘመኔ ካንተ ሌላው መሻቴ ይራቅብኝ ከእኔ *2 መታወቂያዬ ልበልህ መታወቂያዬ መታወቂያዬ ልበልህ የዘላለሜ በአንተ ብቻ ይሁን የኔ ድምዳሜ *2 ባንተ ብቻ ብታወቅ በቅድስናዬ እንዴት መታደሌ ነው ብኖርልህ ጌታዬ እርግፍግፉ ወጥቶ የስጋ ምኞት ሁሌም ባስታዉስ እላይ ያለውን ቤት ሁሌም ባስታውስ የመስቀሉን ሞት ሰዎች ሲጠሩበት ባላቸው በሀብት መታወቂያቸው ሆኖ ምጠፋው ንብረት ለኔ ለታናሹ ገብቶኝ አንድ እውነት አዳኜ ኢየሱስ ሆኖኝ ምልክት መታወቂያዬ እያልኩህ በራሴ ህይወት አንጎራጉራለሁ በቀን በምሽት *2 መታወቂያዬ ልበልህ መታወቂያዬ መታወቂያዬ ልበልህ የዘላለሜ በአንተ ብቻ ይሁን የኔ ድምዳሜ *2
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection