ሀያ አራት ሽማግሌዎች በፊቱ እየሰገዱ ቅዱስ ነህ ቅዱስ እያሉት ሁሉም እያንዳንዱ ጎንበስ ቀና በማለት ዘወትር በእርሱ ፊት ዘላለም ያመጡለታል ቅዱስ መስዋዕት *2 ሰማይንና ምድርን ያለአማካሪ ያበጀ ማነው የሁሉ ፈጣሪ ፍጥረቱ ይናገር ማነው ማሪያቸው ሚንቀጠቀጡለት ፈቅደው ሚገዛቸው *2 ከጌታችን በቀር ማነው ጌታ ስልጣን በእጁ የያዘ ሁሉን የሚረታ ከአምላካችን በቀር ማን ነው አምላክ በፍጥረት አንደበት የሚመለክ ስሙ የከበረ እጅግ የተፈራ በሰማይ በምድር ድንቅን የሚሰራ *2 ማን ነው እስኪ እንደ ጌታ ማን ነው ሁሉን የሚረታ ማን ነው በሃይል የበረታ ማን ነው ማህተሙን የፈታ ማን ነው ያለ በከፍታ ማን ነው ጠላትን የመታ ማን ነው እንደ ኢየሱሴ ማን ነው ከብሮ የነገሰ በየከተማው ላይ ይህ ስም ይጠራ ትውልድን ያድናል ከእሳት መከራ አያከራክርም እንደ ሌላ አማልክት ላመኑበት ይሆናል የመዳን ምልክት *2 ማነው ፈጣሪ የሁሉ መሪ እስኪ የቱ ነው ፍጥረት ይናገር ማነው ይታይ የሁሉ ተካይ የሆነ ኤልሻዳይ በምድር በሰማይ *2 ነገስታት ሁሉ በጊዜያቸው ሁሉም ሲሻሩ የኔ ጌታ ግን ዛሬምኮ አለ በክብሩ የሚሳነው የሚያቅተው አንዳች የለው ሁሉን የገዛ የቻለው ኢየሱስ ነው ኢየሱስ ነው የኛ ጌታ *3 ሁሉን የሚገዛ የጌቶች ጌታ ሞትን የረታ የይሁዳ አንበሳ *2 ስራችንን የሰራ በመስቀል የዋለ በሞቱ አድኖን እንዳንሞት ያረገ እንደ ኢየሱስ/ እንደ አምላኬ የለም ታሪክ የቀየረ በሰማይ በምድር ብቻውን የከበረ ኢየሱስ ነው የኛ ጌታ *3 ሁሉን የሚገዛ የጌቶች ጌታ ሞትን የረታ የይሁዳ አንበሳ *2