በድካሜ እያገዘኝ ያላጣሁት ሁሌ ከጎኔ የሚያኖረኝ በምህረቱ እየሆነኝ መድኃንቴ ወዳጅ አለኝ ብዬ ብጠራው የማላፍርበት እኔስ አለኝ ከማንም ልዩ የሆነኝ አባት የሚገርመኝ ምሕረቱ አቁሞኛል ይሄው ፊቱ የሚደንቀኝ ደግነቱ አኑሮኛል ዛሬም ቤቱ *2 አቁሞኛል ፊቱ *2 የበዛልኝ ምህረቱ አኑሮኛል ቤቱ *2 የበዛልኝ ቸርነቱ ሲገዳደረኝ የጠላቴ ዉጊያ ጌታ አስመልጦኛል ሆኖኝ መሰወርያ ከተዘረጋብኝ ከአደገኛ ወጥመድ አልፌበታለሁ ሆኖልኝ መንገድ ሆኖኛል መንገድ*2 አምልጬ እንድሄድ ሆኖኛል ሕይወት*2 የበዛልኝ ምህረት እንደ አይን ብሌን ስንከባከበኝ ጠላቴ አፍሮ ሲሄድ አየሁኝ አይኔን ከእምባ እግሬን ከዉድቀት አድኖኝ የለ ወይ የርሱ ደግነት ምስጋናዬ ይሰማ ይዉጣ ከአንደበቴ ከሲኦል ለታደገኝ ለዚህ መድኃኒቴ እልልታዬ ይሰማ ይዉጣ ከምላሴ ሞቴን ለሞተልኝ ለደጉ እየሱሴ *2