ልቤ ላይ ምን አለ ዛሬም ያላለቀ *2 እያታለል *2 ይወስዳል ዉሃ እያሳሳቀ *5 የት ነው ያለሁኝ ወዴት እየሄድኩ ነኝ መገኛዬስ የት ነው ራሴን ልጠይቀው *2 ራሴን ልጠይቀው ህይወቴ ምንድነው? ራሴን ልጠይቀው ኑሮዬ ምንድነው? የቆምኩ መስዬ ወድቂያለሁ ወይ ምንድነው ሚታየው ዛሬ ዛሬስ ህይወቴ ላይ ጉልበቴ ደክማለች ምን ሆኖ ፀጋዬ ተንስቶ ሄዷል ቀስ በቀስ ከላዬ *2 አስበኝ አምላኬ ይመለስ ምርኮዬ ህይወቴ ምንድነው? አያለሁ ጓዳዬን *2 እንደወደድከው *8 በአፌ የገባው ወሬና ሃሜት *3 ከስንቱ አስቀረኝ ከአምላክ በረከት *3 በላዬ የበዛው የስጋዬ ኃጢአት *3 እንዳያስቀረኝ ከዘላለም ቤት *3 እንደ ጥላ በሚያልፍ በዚህ ስጋዬ ሕይወቴን እንዳላጣ አስበኝ ጌታዬ የቀረው ዘመኔ ይሁንልኝ በፊትህ ትቀደስ ሕይወቴ ትቀመጥ በቤትህ መድረክ ላይ ስንታይ መስለን እንደ አገልጋይ ሚዛናችን ቀሏል በቃሉ ስንታይ ማንም ባያየን ያየን የለ ጌታ ሰዎች ምን ነካን እንመለስ በቃ *2 አፈር በሚሆነው በዚህ ስጋዬ ሕይወቴን እንዳላጣ አግዘኝ ጌታዬ የቀረው ዘመኔ ይሁንልኝ በፊትህ ትቀደስ ሕይወቴ ትቀመጥ በቤትህ እንደወደድከው/እንደፈለግከው