Song Lyrics

ወዴት ነህ?

Tilahun Goa
Metawekiyaye
ወሰን ያለህ መስሎኝ ለምትገኝበት ብዙ ለፋሁኝ ጌታ ስፍራህን ለማግኘት ውስጤ ሲረጋጋ ቃልህን ሲሰማ በሰማይ ተቀምጠህ ምድርን ምትጫማ ቤትህ ምን አይነት ነው መገኛህ ወዴት ነው *2 ወዴት ነህ? *3 ወዴት ትገኛለህ? አንተ ወሰን የለህ ለካስ በልቤ ዉስጥ አለህ *4 የነፍሴ መሪ ነህ የሕይወቴ ቤዛ ነህ አስፈላጊውን ነገር ላሟላልህና እስኪ ኑርበት ዘላለም ግባና ዓለም ላይ ያለው ብዙ ብዙ ነገር ከአንተ አይለየኝም ከወደድኩህ ፍቅር የነፍሴ ፍላጎት ለአንተ ብቻ መኖር ከአንተ ሌላ አምሮቴ ለዘለዓለም ይቅር አልቻል አለኝ ያላንተ ለራሴ አትችልም ሕይወቴ ከጣችህ ኢየሱሴ አቤቱ አምላኬ አምላኬ ሆይ አትራቅ ለአፍታ ከእኔ አትለይ ደካማ ነው እና አይችልም ጎኔ ከእስትንፋሴ ይልቅ የቅርቤ አንተ ነህ ጌታዬ የልቤ ዛሬም ዛሬም ቢሆን እንዳይደርቁ አጥንቶቼ ታስፈልገኛለህ አትዉጣ ከልቤ *2 ዛሬም ዛሬም ቢሆን እንዳይዝል ጉልበቴ ታስፈልገኛለህ አትሂድ ከቤቴ *2
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection