እገባለሁ ወደ ቤቱ ሳይመሽብኝ ሰዓቱ *2 እገባለሁ ወደ አምላኬ ቤት በዓለም በከንቱ ነገር ስሮጥ እድሜዬ እንዳያልፍ እገባለሁ ወደ አምላኬ እጅ ልጠጋጋውና ላድርገው ወዳጅ *2 በይቅርታ ተቀበለኝ ምሕረትህን አርግልኝ *2 የባዘንኩበት ዘመን በዓለም ወድህ ወዲያ ይብቃኝ ብዬ መጣሁ ዛሬ ወዳንተ ጉያ ልቤን ሰጥቼሃለሁ ላደርግህ ወዳጅ ፊትህን መልስልኝ አርገኝ የአንተ ልጅ *2 በዚህ ወጣትነት ዓለም ከሚገዛኝ ቤትህ ይሻለኛል ምቹ እኮ ነው ደላኝ እፎይ አልኩኝ ጌታ አንተን አመንኩና ኑሮ ጀመርኩብህ በአዲስ ጎዳና *2 ከእንግድህማ የኢየሱስ ነኝ እኔ እርሱም የእኔ ሆኗል ወድጀዋለሁ ላልጣላ ገብቼለታለሁ አዲስ መሃላ *2 ትከሻህ ምቹ ነው የአባትነትህ ልጅህ የተባልኩበት በዝቶልኝ ምሕረትህ እራሴን ፈልገህ ከየት አገኘሀኝ ልረሳው የማልችለው ዉለታህ አለብኝ *2 ከእንግድህማ የኢየሱስ ነኝ እኔ እርሱም የእኔ ሆኗል ወድጀዋለሁ ላልጣላ ገብቼለታለሁ አዲስ መሃላ *2 በይቅርታ ተቀበለኝ ምሕረትህን አርግልኝ *2