ኃያል ሰራዊት ነው በጠላት የማይደፈር ሁሌ ድል ይነሳል በወጣበት መንደር ሃያል ሠራዊት ነው ወገቡን ታጥቆ ግርማው እጅግ ሲያስፈራ መጠኑ ለቆ ኮቴው ሲሰማ ፍርሃት ይጥላል በጠላት መንደር ላይ ሁከት ይፈጥራል *2 የበቀል ሰው ጠላትን የሚጨርሰው አንድ ጊዜ ጠርቶ እሳት የጣለ በበዓል ነቢያት ሰይፉን የሳለ ይገለጥልን እስኪ ይነሳ የጠላት ወገን ትጥቁ ይፈታ *4 እውነት ሲቀበር ነፍሱ ዝም አትልም ኤልዛቤል ሳትሞት ሰላም አያገኝም ሁሉን ድል አድርጎ በገናውን ያነሳል በጠላት መንደር ላይ አምላኩን ያሳያል አንድ ጊዜ ጠርቶ እሳት የጣለ በበዓል ነቢያት ሰይፉን የሳለ ይገለጥልን እስኪ ይነሳ የጠላት ወገን ትጥቁ ይፈታ *4 አላማው አንድ ነው ሌላን አያቀባዥር ግራ ቀኝ አይልም ክፋትን ከመስበር ለእግዚአብሔር ደስታ ሆን ብሎ ይኖራል በዲያብሎስ ቅጥር በቀለን ያዘንባል ጨካኝ ሠራዊት ነው ወገቡን ታጥቆ ግርማው እጅግ ሲያስፈራ መጠኑ ለቆ ኮቴው ሲሰማ ፍርሃት ይጥላል በጠላት መንደር ላይ ሁከት ይፈጥራል የበቀል ሰው ጠላትን የሚጨርሰው አንድ ጊዜ ጠርቶ እሳት የጣለ በበዓል ነቢያት ሰይፉን የሳለ ይገለጥልን እስኪ ይነሳ የጠላት ወገን ትጥቁ ይፈታ *4