ያኔ የተሰጡኝን ቃሎቹን ታምኜ ከሁኔታዎች ላይ ዓይኖቼን አንስቼ አንዳችም ሳልፈራ በትሬን ልዘርጋ የጨለመብኝን እንዳየው ሲነጋ የኪዳኑ ልጅ ነኝ ቃል የተገባልኝ በዚህ ቃል ልገለጥ ታዲያ ምን አሰጋኝ *2 ልገለጥ የአምላኬን ስም ይዤ ልገለጥ በእርሱ ተመርኩዤ ልገለጥ ቃል አለኝ ከጌታ ልገለጥ ዲያብሎስ ይመታ/ ኤልዛቤል ትወጋ * ክፋትና እርኩሰት ምድርን አጥለቅልቆ ብዙ ወገን አልቋል በኃጢአት ላይ ውድቆ በዚህ ነገር ታዲያ ማን ነው ተጠያቂ ለውጥን ላምጣ እንጂ እኔስ ልገለጥ ከእኔ ጋር እንዳለ ተናግሮኛል ጌታ ልግጠመው ጠላቴን በገናዬን/የዕቃ ጦሬን ላንሳ ልገለጥ እርኩሰቷ በዛ ልገለጥ ምድሬን እየገዛ ልገለጥ አለኝ ብዙ ሥራ ልገለጥ ገና የሚሰራ ልገለጥ በጠላት መንደር ላይ ልገለጥ ኃይል አለኝ ከሰማይ ልገለጥ በኤልዛቤል መንግስት ልገለጥ ይብቃት ላዋርዳት የእግዚአብሔርን ነብያት ባስጨረሰችው ላይ እዩ ተገለጠ ታምኖ በአምላኩ ላይ ለውሾች ሰጣት በመስኮት ወርውሮ የአምላኬ እውነት አልቀረም ተቀብሮ ያኔ የነበረው ዛሬም ጉልበታም ነው ጨክኜ ልውጣና ልለፍ አስከብሬው *2 ልገለጥ በሰይጣን መንግስት ልገለጥ በበዓል ነብያት ልገለጥ ጨክኜ ልውጣና ልገለጥ አምላኬን ልጥራና ልገለጥ ማንንም ሳልፈራ ልገለጥ ዋጋ ልክፈልና ልገለጥ ወገቤን ታጥቄ ልገለጥ የስጋዬን ንቄ ልገለጥ ቃል አለኝ ከጌታ ልገለጥ ዲያብሎስ ይመታ/ ኤልዛቤል ትወጋ