Song Lyrics

ለክብሩ ዘምሩ

Tigist Alemu
Maranatha
አዝ፦ ምሥጋናና ክብር ውዳሴና ዕልልታ ይገባሃል አንተ የእኛ ጌታ እግዚአብሔርን የምትወዱ ኦሆ የምትፈሩ አሃ ተነሱ ለክብሩ ዘምሩ (2x) ሠማያዊ ሚስጢር የገለጸላችሁ ከድቅድቅ ጨለማ መጥቶ ያወጣችሁ ይህን እግዚአብሔርን እስኪ እናመስግነው በዝማሬ ዕልልታ ክበር እንበለው አዝ፦ ምሥጋናና ክብር ውዳሴና ዕልልታ ይገባሃል አንተ የእኛ ጌታ እግዚአብሔርን የምትወዱ ኦሆ የምትፈሩ አሃ ተነሱ ለክብሩ ዘምሩ (2x) የምድር ሁሉ ደስታ የፅዮን ተራራ እግዚአብሔር ጥልቅ ነው ክብሩ የሚያስፈራ እንደ እርሱ ያለ አምላክ ከቶ ስላላየን ለታላቁ ጌታ እንሰግድለታለን አዝ፦ ምሥጋናና ክብር ውዳሴና ዕልልታ ይገባሃል አንተ የእኛ ጌታ እግዚአብሔርን የምትወዱ ኦሆ የምትፈሩ አሃ ተነሱ ለክብሩ ዘምሩ (2x) አዲስን ዝማሬ ለእርሱ ዘምሩ ታላቅነቱንም ግርማውንም አውሩ ክብሩን ለአሕዛብ እንናገራለን ተዓምራቱን ደግሞ እኛ እናወራለን አዝ፦ ምሥጋናና ክብር ውዳሴና ዕልልታ ይገባሃል አንተ የእኛ ጌታ እግዚአብሔርን የምትወዱ ኦሆ የምትፈሩ አሃ ተነሱ ለክብሩ ዘምሩ (2x) የእርሱን በጐነት መልካምነቱን ማለዳ ማለዳ ምሕረቱን ካየን በፀጋው በፍቅሩ ጠብቆ ላቆመን ቆመን ከነፍሳችን ምሥጋና እንሰጣለን አዝ፦ ምሥጋናና ክብር ውዳሴና ዕልልታ ይገባሃል አንተ የእኛ ጌታ እግዚአብሔርን የምትወዱ ኦሆ የምትፈሩ አሃ ተነሱ ለክብሩ ዘምሩ (2x) ተነሱ ለክብሩ ዘምሩ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection