Song Lyrics

እግዚአብሔር ሲሰራ

Tigist Alemu
Maranatha
ከአፌ የወጣው ቃል ምንም ሳያፈራ ከቶ አይመለስም ሥራውን ሳይሰራ [1] ብሎ የተናገረው ለሥሙ የሚቀና ገና አሁን እናያለን እግዚአብሔር ሲሰራ (2x) እንደነቃልን እንደነቃልን እግዚአብሔር ሲሰራ በዓይናችን እያየን (2x) በዓይናችን እያየን (4x) ይህ እንዴት ይሆናል ማንስ ያውቅበታል ያስ እንደምን ሆኖ ወደዚህ ይደርሳል በመንፈሱ እንጂ በኃይል የማይሆነው የእግዚአብሔር ሥራ ሁሌም ፍጻሜ አለው (2x) እንደነቃልን እንደነቃልን እግዚአብሔር ሲሰራ በዓይናችን እያየን (2x) በዓይናችን እያየን (4x) እግዚአብሔር የሚያስመካ የሚያስደንቅ የሚያኮራ ሥራው ድንቅ ነው ሲሰራ ሥራው ልዩ ነው ሲሰራ (2x) የሚታመን በአንተ ይታመን የሚመካ በአንተ ይመካ የሚደገፍ በአንተ ይደገፍ የሚኮራ በአንተ ይኩራ እኛስ ኩራት ኩራት ይለናል ይለናል (2x) በአንተ መደገፉ ያስመካናል (2x) የአንተ መሆናችን ያስመካናል (2x) እኛስ ኩራት ኩራት ይለናል ይለናል (2x) በአንተ መደገፉ ያስመካናል (2x) በአንተ መታየቱ ያስመካናል (2x) በአንተ መደገፉ ያስመካናል (2x) በአንተ መታየቱ ያስመካናል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection