Song Lyrics

ልባርክህ

Tigist Alemu
Maranatha
ባከብርህ ባመልክህ ባመሰግንህ ተባረክ ተወደስ ክበር እያልኩህ መቼ ይበቃኛል አንተን ሊገልጽህ ለእኔ ታደረከው ጌታ እየበዛብኝ በተከፋሁ ጊዜ ልቤ ሃዘን ሲውጠኝ አንተ ብቻ ለእኔ ፈጥነህ ደረስክልኝ ከእኔ ጋራ ሆነህ ነፍሴን እያጽናናህ ያንን ጨለማዬን በብርሃንህ አበራህ ስለዚህ ጌታዬ ወዳጄና አባቴ ወዴት እሄዳለሁ ይህን ፍቅር ትቼ (2x) በፊትህ ስበድል በአመጼ ስትቀጣኝ በበደሌ አዝኜ ፊትህን ላይ ስመኝ አይተህ አዘንክልኝ በንስሃ ሞልተህ ጽድቅን አወጣሃት ጠላቴን ረግጠህ ድካሜ ቢበዛ ጉድለቴ ኢየሱስ አንተ ነህ ሙላቴ እንዲሁ በፀጋህ ቆሜያለሁ ሥምህን በዜማ አከብራለሁ (2x) ይገርመኛል ይሄ ፀጋ ይደንቀኛል ይሄ ፀጋ (2x) የዳንኩበት ይሄ ፀጋ የቆምኩበት ይሄ ፀጋ የሚያጽናናኝ ይሄ ፀጋ የሚያስኬደኝ ሃሌሉያ ድካሜ ቢበዛ ጉድለቴ ኢየሱስ አንተ ነህ ሙላቴ እንዲሁ በፀጋህ ቆሜያለሁ ሥምህን በዜማ አከብራለሁ (2x) ይገርመኛል ይሄ ፀጋ ይደንቀኛል ይሄ ፀጋ (2x) የዳንኩበት ይሄ ፀጋ የቆምኩበት ይሄ ፀጋ የሚያጽናናኝ ይሄ ፀጋ የሚያስኬደኝ ሃሌሉያ
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection