አዝ፦ ጌታ አንተ ብቻ እውነተኛ ደስታ በከፍታ በዝቅታ አይወስንህ ሁኔታ አይወስንህ ሁኔታ (2x) ከሠማይ በታች ፍጥረት የሚያገኘው ደስታው የማይጸና የከንቱ ከንቱ ነው ታዲያ ምብዛቱ ጥቅሙ ምንድን ነው ምኞቱ መሻቱ ንፋስ መከተሉ አዝ፦ ጌታ አንተ ብቻ እውነተኛ ደስታ በከፍታ በዝቅታ አይወስንህ ሁኔታ አይወስንህ ሁኔታ (2x) የዚች ዓለም ውብት መቼ ደስታ ይሰጣል ትናንት የነበረ ድንገት ከእጅ ያመልጣል ቋሚ ነገር የለም ለሁሉም ጊዜ አለው የሚጸና ደስታ እግዚአብሔር ብቻ ነው አዝ፦ ጌታ አንተ ብቻ እውነተኛ ደስታ በከፍታ በዝቅታ አይወስንህ ሁኔታ አይወስንህ ሁኔታ (2x) መብዛትን መጉደልን ሁሉ ተምሬያለሁ ኃይልን በሚሰጠኝ ሁሉን እችላለሁ ነገር ተለዋዋጭ መሆኑን አየሁኝ የሚጸና ደስታ ጌታን አገኘሁኝ ደስታዬ አንተ ብቻ ሰላሜ አንተ ብቻ እረፍቴ አንተ ብቻ ሃብቴ አንተ ብቻ (2x) አዝ፦ ጌታ አንተ ብቻ እውነተኛ ደስታ በከፍታ በዝቅታ አይወስንህ ሁኔታ አይወስንህ ሁኔታ (2x)