የገባልኝን ቃል እስከሚፈፅመው እግዚአብሔር ይተጋል እኔም አምነዋለሁ (4x) የገባልኝን ቃል እስከሚፈፅመው እግዚአብሔር ይተጋል እኔም አምነዋለሁ (4x) ፍፁም የማይገባ የማይመስል ነገር እንደምን ይሆናል የተባለ ቢሆን የአብርሃም አምላክ በቃሉ የታመነ እውን ያደርገዋል ተስፋ ከእርሱ ካለ ስለዚህ አምላኬን እጠብቃለሁኝ እርሱ ያየልኝን እኔም እስካየው (2x) ቀናቶች ቢረዝሙ ችግሩም ቢበዛ እምነቴም ቢፈተን ጠላትም ቢነሳ ቃል ተናግሯልና ይሆናል አይቀርም ጌታዬ ሲከፍተው ማንም አይዘጋውም ስለዚህ አምላኬን እጠብቃለሁኝ እርሱ ያየልኝን እኔም እስካየው (2x) ዓይኖቹ ያዩኛል ጆሮውም ይሰማኛል የልቤን ጥያቄ ጌታዬ ያውቀዋል መልስ እስከሚመጣ እስከሚጐበኘኝ አፅንቶ የሚያቆም የተስፋ ቃል አለኝ ስለዚህ አምላኬን እጠብቃለሁኝ እርሱ ያየልኝን እኔም እስካየው (2x)