ስለ ሰው ልጅ ነፍሱን አሳልፎ እስከ መስቀል ታዟልእራሱን አዋርዶ እንዲህ ያለ መውደድ ከወዴት ተሰምቷል? በእግዚአብሔር አብ ፍቃድ በኢየሱስ ተገልጧል (2x) ፍቅር ነው ጌታ ፍቅር ነው ስራው ፍቅር ነው ስሙ ፍቅር ነው (2x) የኃያላን ጉልበት ዝናው ሁሉ ያልፋል ክብሩ ከበሬታው ከንቱ ነው ይቀራል የእኛ ኢየሱስ በግርማ በክብር በኃይል በሞገሱ ፀንቶ የሚኖር (2x) ኃያል ነው ጌታ ኃያል ነው ስራው ኃያል ነው ስሙ ኃያል ነው ፊት አይቶ አያደላ ለሁሉ ነው ወዳጅ የልብ ን የሚረዳ እውነተኛ ፈራጅ ስራው በትክክል ሚዛኑ እውነት ነው በዘመናት ሁሉ በስራው ፃድቅ ነው (2x) ፃድቅ ነው ጌታ ፃድቅ ነው ስራው ፃድቅ ነው ስሙ ፃድቅ ነው (2x) ሌላ ምን እንበልህ ምን እናቅርብ በፊትህ ከማዜም ከመቀኘት በቀር (4x) ለአንተ ነው እንጂ ይኸው ዝማሬ አምልኮ ስግደት ዕልልታ ክብር አሜን ይሁን (2x)