Song Lyrics

ባለፀጋ

Tigist Alemu
Maranatha
አዝ፦ በምሕረቱ ባለፀጋ ከወደደኝ ፍቅሩ የተነሳ ከወደደኝ ፍቅሩ የተነሳ ከክርስቶስ ጋራ ሕይወት ሰጠኝ እንዲሁ በፀጋው አፀደቀኝ (2x) ምንድነው ያቆመኝ ከፃድቃኖች ስፍራ ስለ ምህረትህ ልናገር ላወራ ለካስ ከማህፀን ጌታዬ አስቦኛል ያን ሁሉ ኀጢአቴን በደሙ አጥቦልኛል አዝ፦ በምሕረቱ ባለፀጋ ከወደደኝ ፍቅሩ የተነሳ ከወደደኝ ፍቅሩ የተነሳ ከክርስቶስ ጋራ ሕይወት ሰጠኝ እንዲሁ በፀጋው አፀደቀኝ (2x) እንዴት አደረገኝ እኔን አዲስ ፍጥረት በመንፈሱ ገዛኝ ጌታዬ በእርሱ እምነት ማለዳ ስነሳ ፍቅሩ ትዝ ይለኛል አዲስ ሰው መሆኔ ሁሌም ይደንቀኛል አዝ፦ በምሕረቱ ባለፀጋ ከወደደኝ ፍቅሩ የተነሳ ከወደደኝ ፍቅሩ የተነሳ ከክርስቶስ ጋራ ሕይወት ሰጠኝ እንዲሁ በፀጋው አፀደቀኝ (2x) ፀጋው በእምነት እኔን አድኖኛል የእግዚአብሔር ስጦታ በእርግጥ በዝቶልኛል ታዲያ ምን አለና ከእኔ የምለው ሥራ ታላቅነትህን ደፍሬ ላወራ አዝ፦ በምሕረቱ ባለፀጋ ከወደደኝ ፍቅሩ የተነሳ ከወደደኝ ፍቅሩ የተነሳ ከክርስቶስ ጋራ ሕይወት ሰጠኝ እንዲሁ በፀጋው አፀደቀኝ (2x) እንደ ኀጢአቴ ብዛት ጌታዬ አላረገብኝ እንደ በደሌም ከቶ አልከፈለኝ ጠላቴ ሆይ ስማ እግዚአብሔር ወዶኛል ምሕረት ቸርነቱ ፀጋው በዝቶልኛል አዝ፦ በምሕረቱ ባለፀጋ ከወደደኝ ፍቅሩ የተነሳ ከወደደኝ ፍቅሩ የተነሳ ከክርስቶስ ጋራ ሕይወት ሰጠኝ እንዲሁ በፀጋው አፀደቀኝ (2x) ፍቅሩ በዝቶልኛል ምህረት በዝቶልኛል ፀጋው በዝቶልኛል ሰላም በዝቶልኛል (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection