Song Lyrics

ፍርዱ የማይጓደል

ለአንዱ ሲነጋለት ለአንዱ ሲመሽበት በጠራራው ፀሐይ ቀን ሲጨልምበት የሰው ማንነቱ በገንዘብ ሲለካ ሃያል በጉልበቱ በኃይሉ ሲመካ በገንዘብ ታፍናለት ስትደበቅ የታመነ ወድቆ የቀጠፈ ሲደርቅ የዚህ ዓለም ጉዳይ ፍርድ ጐዶሎ ነው በዘመኔ ታዘብኩ በዐይኖቼ ይህን አየሁ አዝ፦ ፍርዱ የማይጓደል እውነተኛ ዳኛ ቃሉን ያማያጥፍ ታማኝ ጓደኛ በዘመኔ ሁሉ ኢየሱስን ብቻ ልብ ያለው ልብ ይበል እውነት እርሱ ነው እርሱ ነው ሕይወት እርሱ ነው እርሱ ነው መንገድ እርሱ ነው ለመበለቷ በቅን ይፈርዳል የሃዘንተኛውን እንባ ያብሳል ለተገፋው ሰው ለምስኪን አዛኝ የተሰበረውን በቃል ጠጋኝ ይኼ ነው አምላኬ የተመማነኩበት ይኼ ነው ጌታዬ ልቤን የጣልኩበት (2x) ጆሮ ያለው ይስማ ልብ ያለው ይመከር እውነት ሕይወት መንገድ የለም ከእርሱ በቀር (2x) እርሱ ነው ሕይወት እርሱ ነው እርሱ ነው መንገድ እርሱ ነው አዝ፦ ፍርዱ የማይጓደል እውነተኛ ዳኛ ቃሉን ያማያጥፍ ታማኝ ጓደኛ በዘመኔ ሁሉ ኢየሱስን ብቻ ልብ ያለው ልብ ይበል እውነት እርሱ ነው እርሱ ነው ሕይወት እርሱ ነው እርሱ ነው መንገድ እርሱ ነው ያጣ እያገኘ ያገኘም እያጣ የወጣም ወረደ የወረደም ወጣ እንደጊዜው ሆኖ ሕይወት ሲቀያየር ሃያል ጉልበት አጥሮት አንድ ቀን ሲበቀል በሚያልፈው በዚህ ዓለም እንዴት ተስፋ ይጣላል ሸመቆ አይደል አንድቀን ይከዳል የልብ ጓደኛህ እስከሞት የሚወድ ኢየሱስ ብቻ ነው እውነት ሕይወት መንገድ አዝ፦ ፍርዱ የማይጓደል እውነተኛ ዳኛ ቃሉን ያማያጥፍ ታማኝ ጓደኛ በዘመኔ ሁሉ ኢየሱስን ብቻ ልብ ያለው ልብ ይበል እውነት እርሱ ነው እርሱ ነው ሕይወት እርሱ ነው እርሱ ነው መንገድ እርሱ ነው ይኼ ነው አምላኬ የተመማነኩበት ይኼ ነው ጌታዬ ልቤን የጣልኩበት (2x) ጆሮ ያለው ይስማ ልብ ያለው ይመከር እውነት ሕይወት መንገድ የለም ከእርሱ በቀር (2x) እርሱ ነው ሕይወት እርሱ ነው እርሱ ነው መንገድ እርሱ ነው (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection