ያ ሌሊት ትዝ አለኝ (4x) እንዴት ይታለፋል እያልኩ በእኔ ጉልበት በምድር መፈጠሬን የተራገምኩበት ያ ሌሊት ትዝ አለኝ (2x) አንተ ስትመጣ በችግሬ ላይ ጩኸቴን ሰምተህ ስትወርድ ከላይ የማይቻለውን ስትችል እያየሁ ከነፍሴ ዜማ ምሥጋና ኢሄው (2x) አዝ፦ በማለዳ በቀትር በምሽትም ደግሞ በሌሊትም አዲስ ዝማሬ አዲስ ምሥጋና ኢየሱስ ለአንተ ነው ይቅረብልህ ገና (2x) የአምላኬ ጉብኝት ሁልጊዜ??? ደረሰ የምስኪኑን ሰው እንባው ታበሰ ቆሞ አደባባይ ቃኘ በገና ስሙት ሲዘምር አዲስ ምሥጋና (2x) አዝ፦ በማለዳ በቀትር በምሽትም ደግሞ በሌሊትም አዲስ ዝማሬ አዲስ ምሥጋና ኢየሱስ ለአንተ ነው ይቅረብልህ ገና (2x) ያ ሌሊት ትዝ አለኝ (4x) የጨለማው ብርታት የማይነጋ መስሎኝ የጐኔን እንዳላይ ዙሪያዬን ከልሎኝ ያ ሌሊት ትዝ አለኝ (4x) አለቀ ብላ ነፍሴ ስትፈራ የደረስክልኝ ስምህን ስጠራ ጨለማውን ቀን ቀን ያደረግከው ከነፍሴ ዜማ ምሥጋና ይሄው (2x) አዝ፦ በማለዳ በቀትር በምሽትም ደግሞ በሌሊትም አዲስ ዝማሬ አዲስ ምሥጋና ኢየሱስ ለአንተ ነው ይቅረብልህ ገና (2x)