Song Lyrics

ምስጢር

ሚስጥር አለ ልቤ (ሚስጥር ሚስጥር) ለሰው ያልነገርኩት (ሚስጥር ሚስጥር) አብረውኝ ለበሉ (ሚስጥር ሚስጥር) ያላጨዋወትኩት (ሚስጥር ሚስጥር) ዙሪያዬ ጸጥ ሲል (ሚስጥር ሚስጥር) በሮቼን ዘግቼ (ሚስጥር ሚስጥር) ልንገረው ለአምላኬ (ሚስጥር ሚስጥር) የሆዴን ገልጬ (ሚስጥር ሚስጥር) እዩት ይሄ ልቤን እየተሸከመ ብቻውን አምቆት ብቻውን ታምኖ ዛሬ ዙፋኑ ስር ሸክሜን ልጣለው እስከመቼ ልዘን አምላክ እንደሌለው ወዳጅ እንደሌለው አዝ፦ ደረሰ ጊዜው ሰዓቱ የአምላኬን ፊት የማይበት መንፈሴን ላዋርድ እራሴን ዝቅ ይበል ይምበርከክ ጉልበት በስውር የለመንኩትን በግልጽ እርሱ እንደሚከፍለኝ ሸክሜን ልጣል እግሩ ስር መጽሃፍ እንደነገረኝ (2x) ለካስ አለጉዳይ (ሚስጥር ሚስጥር) ለሰው የማይነግሩት (ሚስጥር ሚስጥር) ወይ በሆድ ደብቀው (ሚስጥር ሚስጥር) የማያባብሉት (ሚስጥር ሚስጥር) አምቄ ደብቄ (ሚስጥር ሚስጥር) እስከመቼ ልጐዳ (ሚስጥር ሚስጥር) ልንገረው በእምባዬ (ሚስጥር ሚስጥር) ሰምቶ ለሚረዳ (ሚስጥር ሚስጥር) መጐዳቴን አይቶ ዘምበል ይልልናል ሰምቶ እንዳልሰማ መቼ ጥሎ ያልፋል ለእርሱ እነግረዋለሁ አልፈልግም ለሰው የልቤን ዘርግፌ እገላገላለሁ (2x) አዝ፦ ደረሰ ጊዜው ሰዓቱ የአምላኬን ፊት የማይበት መንፈሴን ላዋርድ እራሴን ዝቅ ይበል ይምበርከክ ጉልበት በስውር የለመንኩትን በግልጽ እርሱ እንደሚከፍለኝ ሸክሜን ልጣል እግሩ ስር መጽሃፍ እንደነገረኝ (2x) አዝ፦ ደረሰ ጊዜው ሰዓቱ የአምላኬን ፊት የማይበት መንፈሴን ላዋርድ እራሴን ዝቅ ይበል ይምበርከክ ጉልበት በስውር የለመንኩትን በግልጽ እርሱ እንደሚከፍለኝ ሸክሜን ልጣል እግሩ ስር መጽሃፍ እንደነገረኝ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection