ያሰቡት ሳይሰምር ሲቀር ሆኖ እንደህልም በእኩለ ቀኑ ላይ በጊዜ ሲጨልም (2x) በዕድሜ ያከማቹት በዋዛ ሲበተን በመከራ እሳት ማንነት ሲፈተን በመከራ እሳት ማንነት ሲፈተን (2x) ጉኔታውን ሳይሆን ቃልህም አምናለሁ ታድናለህ ብዬ ስንቴ ዘምሬያለሁ ወጀቡ ቢበዛም በአንተ ተስፋ አልቆርጥም ይዘምባል እላለሁ ደማነውን ባላይም አዝ፦ (ቀን አለ) ፀሐይ ትወጣለች (ቀን አለ) ይሄ ሌሊት ያልፋል (ቀን አለ) የታመንኩት ጌታ (ቀን አለ) በክብሩ ይመጣል (ቀን አለ) ፀጋ ልኮልኛል (ቀን አለ) እሸጋገራለሁ (ቀን አለ) በአስጨነቀኝ እራስ ላይ (ቀን አለ) ቆሜ እዘምራለሁ (2x) የሕይወት ቀመሩ መውረድና መውጣት ነፍሴ በምድረበዳው ውጊያው ቢያሰለቻት ዐይኖቼ ሳይወዱ ተቀደው ቢያለቅሱ የድል መዝሙሮቼ ሁሉ ዛሬ ቢረሱ እንደማያልፍ የለም ይህን ቀን አልፋለሁ ጌታዬ ሲመጣ በድል እወጣለሁ ይህ ሰው አበቃለት ያለው ጠላቴ ነው በቆፈረው ጉድጓድ ሲወድቅ አየዋለሁ አዝ፦ (ቀን አለ) ፀሐይ ትወጣለች (ቀን አለ) ይሄ ሌሊት ያልፋል (ቀን አለ) የታመንኩት ጌታ (ቀን አለ) በክብሩ ይመጣል (ቀን አለ) ፀጋ ልኮልኛል (ቀን አለ) እሸጋገራለሁ (ቀን አለ) በአስጨነቀኝ እራስ ላይ (ቀን አለ) ቆሜ እዘምራለሁ በወይን ሃረግ ፍሬ ቢታጣ ሚቀመስ ምንም እንኳን ዛሬ ባታፈራ በለስ (2x) በጐች ከማደሪያው ከበረት ቢታጡ እርሾችም ጠውልገው ማዕበልን??? ባይሰጡ (2x) እኔ ግን በእግዚአብሔር በእርሱ ደስ ይለእኛል በከፍታዎችም ላይ ያራምደኛል በመድሃኒቴ አምላክ ሃሴት አደርጋለሁ ጌታ እግዚአብሔር ዘወትር ሃይሌ ነው አዝ፦ (ቀን አለ) ፀሐይ ትወጣለች (ቀን አለ) ይሄ ሌሊት ያልፋል (ቀን አለ) የታመንኩት ጌታ (ቀን አለ) በክብሩ ይመጣል (ቀን አለ) ፀጋ ልኮልኛል (ቀን አለ) እሸጋገራለሁ (ቀን አለ) በአስጨነቀኝ እራስ ላይ (ቀን አለ) ቆሜ እዘምራለሁ (2x) (ቀን አለ)