አንደበት ኖሯቸው ምድርና ሰማይ ምነው ቢናገሩ እንደሌለው መሳይ (3x) እኔስ በዝች ቃሌ በትንሿ አንደበት አልወጣልህ አለኝ ዘምሬ የእርሱን ምህረት የምላኬን በጐነት (አሃሃ) የአምላኬን ቸርነት ጥሩ ቃል ተመርጦ ዜማ ቢደረደር በመልካም አዋቂ አምሮ ቢቀናበር ልሳን ያለው ሁሉ ለአፍታ ሳያባራ አይበቃም ቢዘመር ስለእርሱ ቢወራ (2x) አዝ፦ (አሃሃ) ብቻውን ጌታ ነው (አሃሃ) መለኪያ የለውም (አሃሃ) ፍጥረት ይራመዳል (አሃሃ) እርሱ እንደሚለው (አሃሃ) ይገላል ያድናል (አሃሃ) ይሾማል ይሽራል (አሃሃ) ዐይኖቹን የታል (አሃሃ) ማን ሸሽቶ ይሰወራል ሄይ (6x) ጌታ ነህ ብንለው ሄይ (6x) ሲችል ስላየነው ሄይ (6x) ኤልሻዳይ ብንለው ሄይ (6x) ሲችል ስላየነው አስፈሪው ማዕበል ወጀብ ታዘዘለት ተራራው ለክብሩ ዝቅ ዝቅ አለለት ብቻውን ኤልሻዳይ በሃይል ይገዛል ቢወድም ባይወድም ፍጥረት ይታዘዛል (2x) ሄይ (6x) ጌታ ነህ ብንለው ሄይ (6x) ሲችል ስላየነው ሄይ (6x) ኤልሻዳይ ብንለው ሄይ (6x) ሲችል ስላየነው አጥቢያ ኮከብ ቆመው ፊቱ ሲዘምሩ ሰማያት ሲሰግዱ ሲሞሉ በክብሩ (3x) መስፈሪያም ሲለካ ዙሪያዋን ሲገምት ማን ነበር ያገዘው ምድርን ሲመሰርት (3x) በአደባባዮች ላይ ክህደት ሲዘመር ያወቀ ሲመስለው ሰው ብዙ ሲናገር የለም ያሉት ሄዱ ከነኮተታቸው የእኛ አምላክ ግን አለ በዙፋኑ ይኸው (2x) አዝ፦ (አሃሃ) ብቻውን ጌታ ነው (አሃሃ) መለኪያ የለውም (አሃሃ) ፍጥረት ይራመዳል (አሃሃ) እርሱ እንደሚለው (አሃሃ) ይገላል ያድናል (አሃሃ) ይሾማል ይሽራል (አሃሃ) ዐይኖቹን የታል (አሃሃ) ማን ሸሽቶ ይሰወራል ሄይ (6x) ጌታ ነህ ብንለው ሄይ (6x) ሲችል ስላየነው ሄይ (6x) ኤልሻዳይ ብንለው ሄይ (6x) ሲችል ስላየነው