Song Lyrics

ተነስ

የእስራኤል አምላክ ዛሬም በዙፋኑ ነው (ሆ) ስሙ ሲጠራ ይሰራል አየነው ይኸው (ሆ) በጌትነቱ ችሎት አምኖ ሚስማማ እርሱ አምላኬ ነው የሚል ድምጹን ያሰማ (2x) አዝ፦ ተነስ በገና ሆይ ተነስ ተነስ ማሲንቆ ሆይ ተነስ ተነስ እኔም እነሳለሁ ተነስ አምላኬ እንዲወደስ ተነስ ወንድሜ ሆይ ተነስ ተነሽ እህቴ ሆይ ተነሽ ተነሽ እኔም እነሳለሁ ተነሽ አምላኬ እንዲወደስ ይሰማ አዳዲስ ዜማ በድል ቀን የግል ዝማሬ እንደተባለው አልሆነም ውሸት ነው የጠላት ወሬ የእኛ አምላክ ስሙ ሲጠራ ከሰማይ በእሳት መልሷል ይህንን የሰማ ያያ ኧረ እንዴት ችሎ ይቀመጣል አዝ፦ ተነስ በገና ሆይ ተነስ ተነስ ማሲንቆ ሆይ ተነስ ተነስ እኔም እነሳለሁ ተነስ አምላኬ እንዲወደስ ተነስ ወንድሜ ሆይ ተነስ ተነሽ እህቴ ሆይ ተነሽ ተነሽ እኔም እነሳለሁ ተነሽ አምላኬ እንዲወደስ ተነስ! በልዑል መጠጊያ የሚኖር ሁሉን በሚችል አምላክ ጥላ ውስጥ ያድራል ጥላ ውስጥ ያድራል እግዚአብሔርን አንተ መታመኛዬ ነህ እለዋለሁ አምላኬና መሸሸጊያዬ ነው በእርሱ እታመናለሁ እርሱ ከአዳኝ ወጥመድ ከሚያስደነግጠው ነገር ያድናል በላባዎቹ በላባዎቹ ይጋርደኛል በክንፎቹ በታች ትተማመናለች እውነት (3x) እውነት እንደጋሻ (2x) ይከብበኛል??? በሌሊት ግርማ በቀን ከሚበር ፍላጻ በጨለማ ከሚሄድ ክፉ ነገር ከአደጋና ከቀትር ጋኔን አትፈራም በአተገብህ ሺ በቀኝህ አስር ሺ ይወድቃሉ ወደአንተ ግን አይቀርቡም በዐይኖችህ ብቻ ትመለከታለህ የሃጢአንን ብድራት (2x) ታያለህ አቤቱ አንተ ተስፋዬ ነህ ልዑልን መጠጊያ ያደረጉ ክፉ ነገር ወደአንተ አይቀርብም መቅሰፍትም ወደ ቤትህ አይገባም በመንገድህ ይጠብቁህ ዘንድ መልአክትን ስለአንተ ያዛቸዋል እግርህን በድንጋይ እንዳትሰናከል በእጆቻቸው ያነሱሃል በተኩላና በእባብ ላይ ትጫማለህ አንበሳውና ዘንዶውን ትረግጣለህ በእኔ ተማምኗልና አስጥለዋለሁ ስሜን አውቋልና እጋርደዋለሁ የእስራኤል አምላክ ዛሬም በዙፋኑ ነው (ሆ) ስሙ ሲጠራ ይሰራል አየነው ይኸው (ሆ) በጌትነቱ ችሎት አምኖ ሚስማማ እርሱ አምላኬ ነው የሚል ድምጹን ያሰማ (2x) አዝ፦ ተነስ በገና ሆይ ተነስ ተነስ ማሲንቆ ሆይ ተነስ ተነስ እኔም እነሳለሁ ተነስ አምላኬ እንዲወደስ ተነስ ወንድሜ ሆይ ተነስ ተነሽ እህቴ ሆይ ተነሽ ተነሽ እኔም እነሳለሁ ተነሽ አምላኬ እንዲወደስ የአህዛብ አማልክት በድኖች አይሰሙ ጆሮ እያላቸው ይጥሩት (4x) ተኝቶ ይሆን አምላካቸው የእኔ ግን አምላክ ግን የኤልያስ ስጠራው ከላይ የሰማኝ ተማምኜው ልኑር እንጂ አምኜው ሥጋት አይገባኝ አዝ፦ ተነስ በገና ሆይ ተነስ ተነስ ማሲንቆ ሆይ ተነስ ተነስ እኔም እነሳለሁ ተነስ አምላኬ እንዲወደስ ተነስ ወንድሜ ሆይ ተነስ ተነሽ እህቴ ሆይ ተነሽ ተነሽ እኔም እነሳለሁ ተነሽ አምላኬ እንዲወደስ (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection