አዝ:- በማዕበሉ ላይ ጌታ ነህ ኢየሱስ በወጀቡ ላይ ጌታ ነህ (4x) ያላሰብኩት ቢሆን አሃሃሃ ነገር ቢቀያየር ኦሆሆሆ ተስፋ ያደረኩት አሃሃሃ ሸንበቆው ቢሰበር ኦሆሆሆ ዐይን የሚጣልበት አሃሃሃ አንድ እንኳን ቢጠፋ ኦሆሆሆ ወጀቡ በርትቶ አሃሃሃ ለነገ ቢከፋ ኦሆሆሆ ድምጹን ሳልሰማ የማዕበሉን ሳላይ ያን ሃይል የንፋሱን በሙሉ ልቤ ጠራሃለው ለአንተ የማይሰግድ የማይቆም ማነው አዝ:- በማዕበሉ ላይ ጌታ ነህ ኢየሱስ በወጀቡ ላይ ጌታ ነህ (2x) ቀይ ባሕር ከፊቴ አሃሃሃ ቆሞ ሲያስጨንቅኝ ኦሆሆሆ ፈርንም ከሁአላ አሃሃሃ ሊመጣ ቢውጠኝ ኦሆሆሆ የማመልክህ አምላክ አሃሃሃ ወዴት ነህ እላለሁ ኦሆሆሆ በቃልህ እኔ ቆሜ አሃሃሃ ስምህን እጠራዋለሁ ኦሆሆሆ ጩኀቴን ሰምተህ ከሰማያት እራርተህልኝ እንደአባት መንጥቀህ ስንቴ አውጥተኀኛል የአምናው ለነገ እምነት ሆኖኛል አዝ:- በማዕበሉ ላይ ጌታ ነህ ኢየሱስ በወጀቡ ላይ ጌታ ነህ (4x)