ከቶ አይቸኩልም ዘግይቶ ይነሳል ግን ማንም አይቀድመው ፈጥኖ ይደርሳል በምድረ በዳ ምንጭ የሚያፈልቀው ይሄ ነው እግዚአብሔር የምናመልከው አንተ የምትተኛ ንቃ ተነሳ ክርስቶስ ከላይ ያበራልሃል ሃይል ለሌለው ሃይል ይጨምራል የደከመው መደገፍያ አዝ:- ለደከመው ህይልን ያስታጥቃል የሞተውን በሕይወት ያኖራል ለስልጣኑ ማነው ያልተረታ ዛሬም ነገም የሚያኮራ ጌታ (2x) የሚያኮራ ጌታ የሚያኮራ (4x) የሚያስመካ ጌታ የሚያስመካ (4x) በእሳቱ ውስጥ አለፍኩ አላቃጠለኝም በወንዙ ላይ ቆሜ አላሰጠመኝም ምህረቱ እንደጋሻ ሆኖ እየከለለኝ ጠላቴ ሞቷል ሲል በሕይወት አለሁኝ አዲሱን ዝማሬ ይዤ ወጥችሃለሁ የጠላቴን መንደር አሸብረዋለሁ አምላኬ እንደንስር ሃይሌን አድሶታል ስሙን እየጠራሁ ቀንበር ይሰበራል አዝ:- ለደከመው ህይልን ያስታጥቃል የሞተውን በሕይወት ያኖራል ለስልጣኑ ማነው ያልተረታ ዛሬም ነገም የሚያኮራ ጌታ (2x) የሚያኮራ ጌታ የሚያኮራ (4x) የሚያስመካ ጌታ የሚያስመካ (4x) ቀይ ባሕር ከፊቴ ቆሞ ሲያስጨንቀኝ ሰራዊት እሁአላ ተግቶ ሲከተለኝ እጆቼን አንስቼ አምላኬን ጠራሁኝ ሰመጠ ፈርዖን በዐይኖቼ እያየሁኝ በተዐምር ነው እኮ ጌታ የሚያኖረኝ ስንትን አሳልፎ ቅጥሩን አዘለለኝ ባሕር ተከፍሎልኝ በድል ተሻግሬ አልጠገብኩም ገና ለክብሩ ዘምሬ አዝ:- ለደከመው ህይልን ያስታጥቃል የሞተውን በሕይወት ያኖራል ለስልጣኑ ማነው ያልተረታ ዛሬም ነገም የሚያኮራ ጌታ (2x) የሚያኮራ ጌታ የሚያኮራ (4x) የሚያስመካ ጌታ የሚያስመካ (4x)