አዝ:- ኢትዮጵያ ሀገሬ እጆችሽን የምትዘረጊበት ሰዓቱ ደርሷል እንባ ሚደርቅበት ካፈርሽ ሰላም ይታጨዳል ከወንዝሽ ዓለም ይባረካል ዓለም ይባረካል (2x) አያለሁ አዲስ ቀን ከደመናው ማዶ ብርሃን ሲወጣልሽ ጨለማውን ቀዶ የራቁት ልጆችሽ ይሰበሰባሉ እውነትም እግዚአብሔር ሃያል ነው እያሉ ባማሩት መቅደሶች ወንጌል ይሰበካል ህጻን ሽማግሌው ለአምላክ ክብር ያመጣል እግዚአብሔርም ቃሉን በታምር ያጸናል ሊሰራ ሲወጣ ማን ይቃወመዋል ማን የከለክላል አዝ:- ኢትዮጵያ ሀገሬ እጆችሽን የምትዘረጊበት ሰዓቱ ደርሷል እንባ ሚደርቅበት ካፈርሽ ሰላም ይታጨዳል ከወንዝሽ ዓለም ይባረካል ዓለም ይባረካል እውቀትና ጥበብ ከአምላክ የተዋሉ ኃጢያትን ጠልተው ለጽድቅ የሚኖሩ ልዋይና ዝና ከቶ ማይገዛቸው ለፍርድና ለእውነት ቅናት የበላቸው ልጆች አሉሽ ገና ተግተው የሚነሱ ለምስኪኑ መውደቅ ከልብ የሚሳሱ የተገባልሽ ቃል በእርግጥ ይፈጸማል አምላክሽ ሊያድንሽ ሊታደግሽ ወጥቷል ሊታደግሽ ወጥቷል አዝ:- ኢትዮጵያ ሀገሬ እጆችሽን የምትዘረጊበት ሰዓቱ ደርሷል እንባ ሚደርቅበት ካፈርሽ ሰላም ይታጨዳል ከወንዝሽ ዓለም ይባረካል ዓለም ይባረካል (3x)