ያለፈውን ዘመን ታሪክ አገላብጠን ሕይወትን ግራና ቀኙን ተመልክተን አንድ እውነት ተረዳን ጠንቅቀን አውቀናል እግዚአብሔር ብቻ ነው አምላክ ነህ ብለናል ለተቸገረው ሰው ፈጥነህ የምትደርስ ሲጠሩህ የምትሰማ በእሳት የምትመልስ የኤልያስ አምላክ ዛሬስ መች ደክመሃል በስምህ ተወራርደን ስንቱን ድል አድርገናል አዝ:- ለአምላክነትህ በነፍስ ተወራርደን ሁሉንም ጣልንና አንተን ተከተልን (2x) በዘመናት መሃል በድል ተሻግረናል ልንክደው አንችልም ክንድህን አይተናል ድንቅ ነህ ታደንቀናለህ (4x) ግሩም ነህ ታስገርመናለህ (4x) በችርነትህ አመታትን ለህዝብህ ታቀናጃለህ ምድረ በዳው ስብ ይጠግባል ባሕሩን ታሻግራለህ ከጠላት ዛቻ በሚገርም ታምራትህ ካመለጥን በነፍሳችን ተወራርደን ይገባል አንተን ልናምን አዝ:- ይውጣ እንጂ ያየታሪክ መዝገብ ያደረከው በይፋ ይነበብ እውነት ነው ዘመን ይናገራል እግዚአብሔር ኧረ እንዳንተ የታል (2x) ድንቅ ነህ ታደንቀናለህ (4x) ግሩም ነህ ታስገርመናለህ (4x) ሁሉን ወደ ኋላ ጥለን ተከተልንህ እንደወደድክ አርገህ ይሄው ምራን አልንህ ምች ከሰርን ታዲያ በብዙ አትርፈናል በአንተ እንዳማረብን ጉዑዙ ይናገራል በሚታየው ነገር ሕይወትን ሳንተምን በእምነት ከቃልህ ጋር መራመድ መረጥን ከዚህ ዓለም ክፋት ስምህ አድኖናል ስትደግፈን ያዩ ድንቅ ነህ ብለዋል አዝ:- ለአምላክነትህ በነፍስ ተወራርደን ሁሉንም ጣልንና አንተን ተከተልን (2x) በዘመናት መሃል በድል ተሻግረናል ልንክደው አንችልም ክንድህን አይተናል ድንቅ ነህ ታደንቀናለህ (4x) ግሩም ነህ ታስገርመናለህ (4x)