Song Lyrics

ጌታ እኮ ነህ

Tesfaye Chala
Yebelay Neh Geta
ጌታ እኮ ነው መቃብሬን ከፍቶ ጌታ እኮ ነው በሕይወት ኑር ያለኝ ጌታ እኮ ነው ማነው የሚቃወም ጌታ እኮ ነው ማነው የሚከሰኝ ጌታ እኮ ነው ሸክሜን ከላዬ ላይ ጌታ እኮ ነው ቀንበሬን የሰበረው ጌታ እኮ ነው ክፉውን አልፈራ ጌታ እኮ ነው ቀና ብዬ እሄዳለሁ አዝ:- ጌታ እኮ ነው ኦሆሆ ጌታ እኮ ነው ጌታ ሃ (2x) ጌታ እኮ ነው ይህንን ያደገው ኦሆ (2x) በሥጋ ለባሽ ፊት ስፍራ የሌለው ሰው ሁሉም ከደጃፉ አውጥቶ የጣለው ይሄ ደካማ ሰው በአምላክ ተጐበኘ በጻድቃን ጉባዔ ሲዘምር ተገኝ አትሉም ወይ ታዲያ ኢየሱስ ጌታ ነው (2x) ምስኪኑን ከአምድ ላይ አንስቶ አከበረው (2x) ያልቀመሰ ማነው ምህረት ቸርነቱን (2x) እስቲ በምሥጋና እንሙላው መቅደሱን (2x) አዝ:- ጌታ እኮ ነው ኦሆሆ ጌታ እኮ ነው ጌታ ሃ (2x) ጌታ እኮ ነው ይህንን ያደገው ኦሆ (2x) የሜበሉን ብርታት ወጀቡን አይቼ (2x) ወየሁ ጠፋሁ በቃ እያልኩኝ ፈርቼ (2x) ሞት እያጣጣረኝ አምላኬን ጠራሁኝ ኢየሱሴን ጠራሁኝ ወጥመድ ተሰበረ ከሞት አመለጥኩኝ (2x) ጌታ እኮ ነው መቃብሬን ከፍቶ ጌታ እኮ ነው በሕይወት ኑር ያለኝ ጌታ እኮ ነው ማነው የሚቃወም ጌታ እኮ ነው ማነው የሚከሰኝ ጌታ እኮ ነው ሸክሜን ከላዬ ላይ ጌታ እኮ ነው ቀንበሬን የሰበረው ጌታ እኮ ነው ክፉውን አልፈራ ጌታ እኮ ነው ቀና ብዬ እሄዳለሁ አዝ:- ጌታ እኮ ነው ኦሆሆ ጌታ እኮ ነው ጌታ ሃ (2x) ጌታ እኮ ነው ይህንን ያደገው ኦሆ (2x) ሥሙን ተጣርቼ ከቶ አፍሬ አላውቅም (2x) ጠላት ቢፎክርም ልቤ አይደነግጥም (2x) አምላኬን ታምኜ ቅጥሩን እዘላለሁ (2x) ስሙን እያወደስኩ ገና እኖራለሁ (2x) አዝ:- ጌታ እኮ ነው ኦሆሆ ጌታ እኮ ነው ጌታ ሃ (2x) ጌታ እኮ ነው ይህንን ያደገው ኦሆ (2x) ጌታ እኮ ነው ኦሆሆ ጌታ እኮ ነው ጌታ ሃ (2x) ጌታ እኮ ነው ይህንን ያደገው ኦሆ (6x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection