አዝ:- ከለለኝ (6x) ከለለኝ በምህረቱ ከለለኝ በቸርነቱ ከለለኝ በደግነቱ ከለለኝ በበጐነቱ ከለለኝ በምህረቱ ከለለኝ በቸርነት ከለለኝ በደግነቱ ከለለኝ በበጐነቱ (2x) ጠላቴ ሊያጠፋኝ ወጥመዱን ዘርግቶ (አሃ አሃ ወጥመዱን ዘርግቶ) ከግራና ከቀኝ የሚረዳኝ ጠፍቶ (አሃ አሃ የሚረዳኝ ጠፍቶ) ወደ ተራሮች ላይ ዓይኖቼን ባነሳ (አሃ አሃ ዓይኖቼን ባነሳ) ረዳት ከወዴት ይምጣ ሰው ሁሉ ሲረሳኝ (አሃ አሃ ሰው ሁሉ ሲረሳኝ) የማይረሳ አምላክ ድንገት ያስባል ምስክሩ ነኝ እኔን ረድቶኛል ሰማይን ቀዶ ወርዶ አሳረፈኝ አባት አለኝ ልበል እንዴት ደስ አይለኝ (2x) አዝ:- ከለለኝ (6x) ከለለኝ በምህረቱ ከለለኝ በቸርነቱ ከለለኝ በደግነቱ ከለለኝ በበጐነቱ ከለለኝ በምህረቱ ከለለኝ በቸርነት ከለለኝ በደግነቱ ከለለኝ በበጐነቱ ቀድሞኝ እየወጣ ከፊት ፊት ሲመራኝ (አሃ አሃ ከፊት ፊት ሲመራኝ) አልረሳም ካችሃምና እንዴት እንደረዳኝ (አሃ አሃ እንዴት እንደረዳኝ) እንደ ዐይኖቹ ብሌን ተተንቅቆልኛል (አሃ አሃ ተጠንቅቆልኛል) አፌን ሞልቼ ልበል እግዚአብሔር ያድናል (አሃ አሃ አምላኬ ያድናል) ውዴን ተደግፌ ወጣሁ ከበረሃ ዙሪያዬን አጠረው ደስታና ፍሰሃ የማምለጫ አለት ጽኑ ግንብ ሆኖኛል ጥበቃውን ሳስብ ዘምር ያሰኘኛል (2x) አዝ:- ከለለኝ (6x) ከለለኝ በምህረቱ ከለለኝ በቸርነቱ ከለለኝ በደግነቱ ከለለኝ በበጐነቱ ከለለኝ በምህረቱ ከለለኝ በቸርነት ከለለኝ በደግነቱ ከለለኝ በበጐነቱ