ቀኑ እንዴት ይገፋል ያለመጨነቅ በሃሳብ ማጥ ውስጥ መማቀቅ (2x) ሳይሞላለት ዛሬን ነገን ሲፍጨረጨር በሥጋት ብዛት ሲወጠር (2x) የሰው ሕይወት በምድር ሰልፉ እንዴት ብርቱ ነው ማነው ከዚህ መዓት የሚገላግለው አዝ:- የሁሉ ቁልፍ በእጁ ያለው መፍትሄው ኢየሱስ ብቻ ነው (2x) ኢየሱስ (፲2x) የሁሉን ሚስጥር ቁልፉን ይዘሃል በአሰራርህ ማን ይመስልሃል በሰማይ በምድር ስልጣን የአንተ ነው እንዲህ አታድርግ የሚልህ ማነው ሕይወትም በድንገት ሲለብስ ደመና ደጅ ሲወጣ ገበና (2x) ያላሰቡት ሲደርስ ያሰቡት ሳይሞላ ሰው ከእርሱ ጋር ሲጣላ (2x) የሰው ሕይወት በምድር ሰልፉ እንዴት ብርቱ ነው ማነው ከዚህ መዓት የሚገላግለው አዝ:- የሁሉ ቁልፍ በእጁ ያለው መፍትሄው ኢየሱስ ብቻ ነው (2x) ኢየሱስ (፲2x) የሁሉን ሚስጥር ቁልፉን ይዘሃል በአሰራርህ ማን ይመስልሃል በሰማይ በምድር ስልጣን የአንተ ነው እንዲህ አታድርግ የሚልህ ማነው