እንዳለፈ ውኃ መከራዬን አስረሳኝ በጠላቶቼ ፊት እራሴን በዘይት ቀባ ኧረ እንዴት ይበዛል ሌት ተቀን ባከብረው ማንም የማይመስለው ወዳጅ አግኝቻለሁ (4x) አሃ የጠላቴ ዛቻ አሃ አይ ማስፈራራቱ አሃ ከንቱ ሆኖ ቀረ አሃ ቀደመች ምህረቱ አሃ ሌሊት በእሳት አምድ አሃ በደመና መራኝ አሃ እረ ማነው ከልካይ አምላኬ ከረዳኝ እረ ማነው ከልካይ ኤልሻዳይ ከረዳኝ አዝ:- አደረገልኝ ተዐምር አደረገልኝ (2x) ተራራዬን ናደው ናደው ሸለቆዬን ሞላ ሃሃ ባሕሩን ከፈለው ኦሆሆ መንገዴን አቀና (2x) ዘይት ከማሰሮ ከማድጋው አልቆ ተስፋዬ ተሰብሮ ተሰባብሮ ደቆ ስሙን ተጣርቼ የልቤን ስነግረው እፌን ሞልቶ በሳቅ ሕይወቴን አዳነው የአምናው ችግር ሄደ ማድጋው ሙሉ ነው ከእርሴ ተርፌ አለኝ የምሰጠው የተዐምራት አምላክ ተዐምር አድርጐልኛል ፍጥረት ሁሉ ይስማው ነገር ተገልብጧል አዝ:- አደረገልኝ ተዐምር አደረገልኝ (2x) ተራራዬን ናደው ናደው ሸለቆዬን ሞላ ሃሃ ባሕሩን ከፈለው ኦሆሆ መንገዴን አቀና (2x) አሃሃ አዲስ ቅኔ ላምጣ አሃሃ ላክብረው ሳልቆጥብ አሃሃ እግሮቼም ይዝለሉ በፊቱ ላሸብሽብ አሃሃ ክብሬን ብጥልለት አሃሃ የሚንቀኝ ማነው አሃሃ ያደረገልኝ እኔ ነኝ የማውቀው አሃሃ የተሰራልኝን እኔ ነኝ የማውቀው ሰማይ ጥርት አለ ደመናውም ጠፋ የችግሩ ብርታት በፊቴ ለቆ ጠፋ የነበረው ሄደ ያለውም አለቀ ውኃ ሳይኖርበት ሸለቆው ደረቀ ደመናም ሳይታይ ንፋስም ሳይነፍስ ዝናባትን አዞ ምድርን ሲያረሰርስ የጠላቴን እቅድ እያፈረሰልኝ ድል በድል ላይ እመድኩ ድንቅ አደረገልኝ አዝ:- አደረገልኝ ተዐምር አደረገልኝ (2x) ተራራዬን ናደው ናደው ሸለቆዬን ሞላ ሃሃ ባሕሩን ከፈለው ኦሆሆ መንገዴን አቀና (2x)