Song Lyrics

የበላይ

Tesfaye Chala
Yebelay Neh Geta
ከአንተ ጋር የሚቆም ደፍሮ የሚወዳደር (የበላይ አሃሃ የበላይ) አልተገኘም በምድር ከጫፍ ጫፍ ቢቆጠር (የበላይ አሃሃ የበላይ) ሥምህ ብቻ አይደለም ሥራህ ይናገራል (የበላይ አሃሃ የበላይ) የትኛው ጀግና ሰው መቃብር ፈንቅሏል (የበላይ አሃሃ የበላይ) (2x) አዝ:- የበላይ ነህ ጌታ የበላይ የሁሉ በላይ በላይ (3x) የበላይ የሁሉ በላይ (2x) የበላይ የሁሉ በላይ (4x) ብዙ ሃያላንን በምድር ላይ አይተናል ማኅደር ሲገለጥ ታሪክ አንብበናል የትኛው ጀግና ነው ሞትን ያሸነፈው ስንቱን ወንድ አይደል ወይ መቃብር የዋጠው አንተ ግን ከፍ ብለሃል ሞትና መውጊያውን ሰብረሃል ልኩራ እንጂ በአንተ እንዴት ልፈር ጌታ ነህ ታሪክ ይናገር (2x) አዝ:- የበላይ ነህ ጌታ የበላይ የሁሉ በላይ በላይ (3x) የበላይ የሁሉ በላይ (2x) የበላይ የሁሉ በላይ (4x) እስቲ ይናገሩ ሰማይና ምድር (የበላይ አሃሃ የበላይ) የታሪክ አዋቂ ይጠራ/አምጡልኝ ምስክር (የበላይ አሃሃ የበላይ) ከአንተ/ከእኔ በላይ ጌታ ሞትን ድል ያደረገ (የበላይ አሃሃ የበላይ) እረ ማነው እርሱ በክብር ያረገ (የበላይ አሃሃ የበላይ) (2x) አዝ:- የበላይ ነህ ጌታ የበላይ የሁሉ በላይ በላይ (3x) የበላይ የሁሉ በላይ (2x) የበላይ የሁሉ በላይ (4x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection