Song Lyrics

እግዚአብሔርን በእውነት ለሚወዱት

Tesfaye Chala
Wetimedu Tesebiro Ameletiku
አዝ፦ እግዚአብሔርን በእውነት ለሚወዱ እንደ ሀሳቡም ደግሞ ለተጠሩ ነገር ሁሉ ለበጐ እንዲደረግ እናውቃለን ይሄን እናውቃለን (4x) በምድር ሰልፍ ሲያይል ሲበረታ ያመኑትም ቃልኪዳኑ ሲፈታ መውጫው ጠፍቶ ቀኑ ሲጨላልም መባረኪያው ዘመኑ ሲረዝም ጌታን ታምኖ በአንዳች ሳይጨነቅ በወጀቡ ፈርቶ ስፍራን ሳይለቅ ማን ነው እርሱ በእግዚአብሔር ያረፈ መከራውን በደስታ ያለፈ (2x) አዝ፦ እግዚአብሔርን በእውነት ለሚወዱ እንደ ሀሳቡም ደግሞ ለተጠሩ ነገር ሁሉ ለበጐ እንዲደረግ እናውቃለን ይሄን እናውቃለን እናምናለን ይሄን እናምናለን (3x) በአንበሶች ጉድጓድ መጣል መርጦ የአንብን ማስፈራራት ረግጦ ከልቡ ነው ለአምላክ ያደረሰው ብርቱ ነፋስ ያላንገዳገደው አልበላው አውሬው አንደዋዛ በክብሩ ያ ሰው ተገዛ ቢመስል እንኳን እግዚአብሔር የጣለው የሚሆነው ሁሉም ለበጐ ነው (2x) አዝ፦ እግዚአብሔርን በእውነት ለሚወዱ እንደ ሀሳቡም ደግሞ ለተጠሩ ነገር ሁሉ ለበጐ እንዲደረግ እናውቃለን ይሄን እናውቃለን (2x) እንሰብካለን ይሄን እንሰብካለን (2x) ቢያሰለችም የምድር ውጣ ውረድ ሌላው ሲከብር አንተ ብትዋረድ ብርሃኑ ቶሎ ቢመሽብህ የታመንከው ድንገት ቢርቅብህ ያስብሃል ጌታ በሞገሱ አካሎችህ መከራ እስኪረሱ አትከፋ በአምላክ ፀጋ ቻለው አይጥልህም እግዚአብሔር ቀን አለው (2x) አዝ፦ እግዚአብሔርን በእውነት ለሚወዱ እንደ ሀሳቡም ደግሞ ለተጠሩ ነገር ሁሉ ለበጐ እንዲደረግ እናውቃለን ይሄን እናውቃለን እንሰብካለን ይሄን እንሰብካለን እናምናለን ይሄን እናምናለን (2x)
Mezmur debter

Ethio Christian Lyrics Collection